ኢትስዊች አክስዮን ማህበር ከ740 ቢሊየን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር አደረገ

Date:

ይህ የገንዘብ ዝውውር በ2መቶ87 ሚሊየን በላይ ግብይት የተፈፀመ ነው። ከዚህ ውስጥ ከ5መቶ77 ቢሊየን ብር በላዩ፥128.3 ሚሊየን ከአንድ የፋይናንስ ተቋም ወደ ሌላ በተደረገ የገንዘብ ማስተላለፍ የተዘዋወረ መሆኑ ተገልጿል።

ኩባንያው ይህን ያለው በ12ኛው የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ነው።

የኢትስዊች አክስዮን ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ደስታ፤ የ1ሺህ ብር አክስዮን የትርፍ ድርሻ ወደ ብር 4መቶ86 አድጓል ብለዋል።

የኩባንያው አጠቃላይ የተከፈለ ካፒታል ከ 2 ቢሊየን 5መቶ ሚሊየን መሻገሩን ተናግረዋል።

የቦርድ ሰብሳቢው የኩባንያው አመታዊ ገቢ ብር 2.2 ቢሊየን መድረሱን አስታውቀዋል።

ከታክስ በፊት ኩባንያው ያገኘው ትርፍ 1.42 ቢሊየን ብር ሆኗል ብለዋል።

በግል እና በመንግስት ሁሉም ባንኮች እንዲሁም በብሔራዊ ባንክ ባለቤትነት የሚተዳደረው አክስዮን ማህበሩ፤ በፋይናንስ ተቋማት፣ በአገር ውስጥ የክፍያ ስርዓት እና በብሔራዊ የክፍያ ስርዓት መካከል የእርስ በርስ የገንዘብ ዝውውር ስርዓት እንዲኖር ለማድረግ ይገደዳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሜሪጆይ ኢትዮጵያ 10,000 የአሜሪካ ዶላር ተበረከተለት

የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የሁልጊዜ ደጋፊ ዩስትሬት ፓርኪንግ (UStreet parking)...

ዶክተር ጌታቸው ተድላ ሁለት መፅሐፍትን ያስመርቃሉ

ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በዶክተር ጌታቸው ተድላ አበበ...