ኢትዮጵያዊው የፊልም ባለሙያ ቤዛ ኃይሉ ‘አላዛር’ በተሰኘ ፊልም ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸነፈ::
በፊልም ጽሁፍ አዘጋጁና ዳይሬክተሩ የተሠራው ፊልም፤ የ “ዳካር ኮርት የ2025 ዓለም አቀፍ የአጭር ፊልም ፌስቲቫል ግራንድ ፕሪ ሽልማት አሸናፊ ለመሆን በቅቷል፡፡
ለ36 ደቂቃዎች የሚዘልቀው “አላዛር” ፊልም፣ ለምርጥ ዳይሬክተር የሚሰጠውን “አባባካር ሳም ማክሃራም” የተሰኘውን ሽልማት መቀዳጀቱንም አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡
ፊልሙ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ የገበሬ ማህበረሰብ ሐይማኖት፣ አመክንዮና አምልኮ ዙሪያ በማጠንጠን ተመልካቾችን ስሜታዊ መዋዥቅ ውስጥ ሰቅዞ እንደሚይዝ ዳኞቹ ለምርጫቸው በሰጡት ማብራሪያ መናገራቸውን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
