ታዋቂው ቢሊየነር ጃክ ማ በአፍሪካ ስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት ባቋቋሙትና በጠቅላላው የ1.5 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት በሚያበረክተው Africa’s Business Heroes (ABH) መድረክ ላይ ኢትዮጵያዊው የቴክኖሎጂ ይዘት ፈጣሪ ጆኤል ጣልአርጌ (Joel Talargie) ሀገራችንን በኩራት ወክሏል፡፡
ጆኤል በዚህ ታላቅ አህጉራዊ መድረክ ላይ አለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪ (International Influencer) ሆኖ የተጋበዘ ሲሆን፣ በዝግጅቱ ላይ በዚህ ደረጃ የተሳተፈ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ይሄም ለሁለተኛ ጊዜ ነዉ።
የሚገርመው ግን የጆኤል ስኬት የጀመረው በገዛ መኝታ ቤቱ ውስጥ በአንድ ስልክ የሞባይል ዳታ በማይሰራ ስልክ ነበር። ከብዙ ጥረት በኋላ ጆኤል የቴክኖሎጂ ስራዎቹን በማሳደግ ዲጂታል ኮንስትራክት የተባለ ድርጅት መስራች መሆን የቻለ ሲሆን፤ ድርጅቱም በብዙ ቋንቋዎች የሚሰሩ በAI የታገዙ ድረ-ገጾችን፣ የ24/7 AI ቻትቦቶችን፣ ዲጂታል ማርኬቲንግና ለንግድ ቤቶች የQR ኮድ ሜኑዎችን በማቅረብ ላይ ይገኛል።
አቤል ብርሃኑ ባዬ-
