ኢትዮጵያ የፀረ- ተህዋስያን መድሀኒት መቋቋምን ለመዋጋት አራተኛውን ሀገር አቀፍ ዕቅድ አስጀመረች

Date:

ኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ለመከላከል ያላትን ቁርጠኝነት በማረጋገጥ የፀረ- ተህዋስያን መቋቋምን ለመዋጋት ያለመውን አራተኛውን አገርአቀፍ የድርጊት መርሃ ግብር ማስጀመሯን በአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ) ገለፀ።

የድርጊት መርሃግብሩ ኢትዮጵያን፣ ባክቴሪያዎች፣ ቫይረሶች፣ ፈንገሶች እና ጥገኛ ተህዋስያንን ለመግደል በተዘጋጁ መድኃኒቶች ላይ ተህዋስያኑ የመከላከል አቅም ሲያዳብሩ የሚከሰተውን የፀረ- ተህዋስያን መድሀኒት ተከላካይነትን ለመቋቋም የተዋቀሩ ስልቶች ካሏቸው የአፍሪካ አገራት ተርታ እንድትሰለፍ ያደርጋታል ተብሏል።

ተነሳሽነቱ በአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ)፣ በዓለም ጤና ድርጅት፣ በተባበሩት መንግስታት የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO)፣ በዩናይትድ ኪንግደም የጤና ደህንነት ኤጀንሲ (UKHSA)፣ በዓለም ባንክ እና በምሥራቅ፣ መካከለኛውና ደቡባዊ አፍሪካ ጤና ማህበረሰብ (ECSA-HC) ድጋፍ ተደርጎለታል።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በዓለም የፀረ- ተህዋስያን መድሀኒት ተከላካይነት ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት ወቅት በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት ላይ “በዓለም ዙሪያ መድሀኒትን የሚከላከሉ ተህዋስያን እየጨመሩ ነው። ወሳኝ እርምጃዎች ካልተወሰዱ፣ በ2050 ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚውን አንድ ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር ግምት ያለው ኪሳራ የሚያስከትል የ70 በመቶ የፀረ- ተህዋስያን መድሀኒት ተከላካይነት ተጽዕኖዎች መጨመር ልንመለከት እንችላለን” ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም የፀረ- ተህዋስያን መድሀኒት ተከላካይነት “አስቸኳይ እና የተቀናጀ እርምጃ የሚጠይቅ እያደገ የመጣ ቀውስ” ሲሉ ገልጸውታል።

የአፍሪካ ሲዲሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ራጂ ታጁዲን ማስጠንቀቂያውን አስተጋብተዋል። አንቲማይክሮቢያል ተከላካይነትን “ከእንግዲህ ዝምተኛ ወረርሽኝ አይደለም” እና ከዓለማችን አሥሩ ከፍተኛ የሕዝብ ጤና ስጋቶች መካከል አንዱ ነው ሲሉም ገልጸውታል።

የአፍሪካ ሲዲሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ራጂ ታጁዲን በበኩላቸው ይሄንኑ ስጋት አስተጋብተዋል። የፀረ- ተህዋስያን መድሀኒት ተከላካይነት “ከእንግዲህ ዝምተኛ ወረርሽኝ አይደለም” ሲሉ ገልፀው ከዓለማችን አሥሩ ከፍተኛ የሕዝብ ጤና ስጋቶች መካከል አንዱ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

አፍሪካ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ከፀረ- ተህዋስያን መድሀኒት መቋቋም ጋር የተያያዙ ሞቶችን ታስተናግዳለች። ይህ ቁጥር ከዓለም አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 21 በመቶ ያህሉን የሚሸፍን ነው። ፈጣን ጣልቃገብነት ከሌለ፣ በ2050 የሟቾች ቁጥር በዓመት ወደ 4.1 ሚሊዮን ሊደርስ ይችላል፣ ይህም በተላላፊ በሽታ መቆጣጠር ላይ የተገኙትን ስኬቶች ወደ ኋላ የሚቀለብስ መሆኑ ተጠቁሟል።

አፍሪካ ሲዲሲ ኢትዮጵያ ያስጀመረችው አዲሱ መርሃግብር አህጉራዊ አመራርን ያሳያል ብሏል። ሆኖም ቀጠናዊ እድገት ይመዝገብ እንጂ፣ ምርመራና መድኃኒቶችን ለማግኘት ያለው ውስን አቅም፣ በቂ ባልሆነ የገንዘብ ድጋፍ የሚከናወኑ የድርጊት መርሃ ግብሮች፣ ደካማ የኢንፌክሽን መከላከያ ሥርዓቶች እንዲሁም የተበታተነ የህክምና ክትትልን የመሳሰሉ ፈተናዎች አሁንም መኖራቸው ተመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...