እስራኤል ሀማስ ትጥቅ ይፈታ አለች

Date:

የእስራኤል ጦር ጋዛን መክበቡን ተከትሎ ሀማስ እጅ  እንዲሰጥ የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጥሪ አቀረቡ።

በጋዛ ጥቃቱን አጠናክሮ የቀጠለው የእስራኤል ጦር  በርካታ ፍልስጤማውያን መጠለያ ፍለጋ እንዲሰቃዩ አድርጓል ተብሏል።

የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ጌዲዮን ሳር  በኢየሩሳሌም በሰጡት መግለጫ ሀማስ ታጋቾችን የሚለቅ እና ትጥቁን የሚፈታ ከሆነ ጦርነቱ አሁን ሊቆም ይችላል  ብለዋል።

ጌዲዮን አክለውም እዚህ ግብ ላይ መድረሳችን ከደስታ በላይ የሆነ እና የፖለቲካ ጥቅማችንን ያስከበርንበት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የሚኒስትሩን መግለጫ ተከትሎ የሀማስ ከፍተኛ ባለስልጣን ባሲም ናኢም እስራኤል ከጋዛ ጦሯን የምታስወጣ ከሆነ ሁለንም ታጋቾ እንደሚፈቱ ገልጸው፤ ትጥቃቸውን ግን ከቶም እንደማያወርዱ ተናግረዋል።

ባለፈው ወር እስራኤል ጋዛን ሙሉ በሙሉ ለመያዝ ዘመቻ መጀመሯ የሚታወስ ሲሆን አሁን ላይ የጋዛ ከተሞችን በመቆጣጠር ትምህር ቤቶችን ፤ የጤና ተቋማትን ስታወድም በርካታ ንጹሀንም መገዳለቸውን ሀማስ የሚመራው የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ሁለት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ቀናት የቀሩት የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት የመካከለኛው ምስራቅ ቀጠናን ረፍት አልባ በማድረግ ፤በርካታ ንጹሀን ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጓል።

ሮይተርስ እና አሻራቅ አል- አውሳት ዘግበውታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...