በድብደባው ሁለት ሰዎች ሲሞቱ አምስት መቁሰላቸውን ሑቲዎች የሚቆጣጠሩት መገኛ ብዙኃን አስታውቋል።
እስራኤል ዛሬ ያካሄደችው ድብደባ በኢራን «ይደገፋሉ» የምትላቸውን የሁቲ አማፅያን ትላንት በእስራኤል ላይ ለፈጸሙት የሚሳይል ጥቃት የበቀል ምላሽ ነው ተብሏል።
የሁቲ አማፅያን ወደ እስራኤል የተኮሱትና በእስራኤል ጦር የከሸፈው ሚሳይል ከዚህ ቀደም ይተኩሱት ከነበረው የተለየ መሆኑን አስታውቃለች።
በዛሬው የእስራኤል ጥቃት የሁቲ አማፅያን ወታደራዊ ተቋማት ላይ ዒላማ ያደረገ እንደነበር የእስራኤል ጦር አስታውቋል። ስለደረሰ ጉዳት ግን እስከአሁን የተሰጠ ዝርዝር መረጃ የለም።
የሁቲ የመገናኛ ብዙሃን ምክትል ሃላፊ ነስረዲን አሚር ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት «የእስራኤል ጥቃት አያንበረክከንም፤ በእስራኤል ላይ ጥቃት መፈጸማችን እንቀጥላለን» ማለታቸውን የዜና ወኪሉ ዘግቧል።
