ኦፕሬሽን ኢትዮጵያ ለመቄዶንያ ለ4ኛ ጊዜ የአይን ህክምና አገልግሎት ሰጠ

Date:

የእስራኤል የሕክምና ተቋም የሆነው ኦፕሬሽን ኢትዮጵያ፣ ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር ለ4ኛ ጊዜ የአይን ሕክምና አገልግሎት ሰጠ።

ተቋሙ ሕዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም በመቄዶንያ ማዕከል በመገኘት የአይን ሕክምና ለሚያስፈልጋቸው ከ500 በላይ ታማሚዎች የተለያዩ የአይን ሕክምና አገልግሎቶችን ሰጥቷል። በተጨማሪም የአይን መነጽር ለሚያስፈልጋቸው ወደ 300 ለሚጠጉ ሕመምተኞች መነጽር አበርክቷል።

 

አገልግሎቱ መቄዶንያ በአይን ሕክምና ዙሪያ የነበረበትን ከፍተኛ የተደራሽነት ችግር ለማቃለል ትልቅ ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር፣ ኦፕሬሽን ኢትዮጵያ የቦታ ርቀት ሳይገድበው በየዓመቱ ወደ ማዕከሉ በመምጣት ለሚያከናውነው የበጎ ተግባር አድናቆቱን ገልጿል። በተለይም ለተቋሙ መስራችና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ሞሪስ ሃርትስቲንና ለባለቤታቸው ላሳዩት ፍቅርና ደግነት፣ በማዕከሉ ከሚታገዙ ከ9 ሺህ በላይ ወገኖች ስም ጥልቅ ምስጋናውን አቅርቧል።

 

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የመምህራንን ደመወዝ የሚያዘገዩ መዋቅሮች ተጠያቂ እንዲሆኑ እንደሚደረግ ተገለጸ

3ኛው ክልል አቀፍ የትምህርት ሴክተር ጉባኤ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ነገ በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመጪው ሐሙስ ህዳር 17...

ከፍተኛ የወጪ ንግድ ገቢ ያስመዘገቡ ድርጅቶች ተሸለሙ

በጥራጥሬና ቅባት እህሎች ዘርፍ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገቢ ያስገኙ...

ዓለም አቀፉ ሽልማት ለጋዜጠኛ ይስሐቅ በላይ ተሰጠዉ

ዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ (IOC) በ4ኛው የዓለም የወጣቶች ኦሎምፒክ...