‹‹ከሰራተኛነት ወደ ሥራ ፈጣሪነት አስተሳሰብ ተሸጋግሬአለሁ››

Date:

መድኃኒት ሾቶቶ

የ28 ዓመት ወጣቷ መድኃኒት ሾቶቶ ባለትዳር እና የአንድ ልጅ እናት ናት፡፡ አሁን ላይ ኑሮዋን በዲላ ከተማ ያደረገችው ወጣቷ ገቢ የሚያስገኝላትን ሥራ ለማግኘት በእጅጉ ትፈልግ ነበር፡፡ እናም ‹‹ዩዝ ኤንድ ካልቸራል ፋውንዴሽን›› በሚያካሔደው የማኅበረሰብ ንቅናቄ ወቅት መድኃኒት ከፋውንዴሽኑ የ‹‹ከፍታ›› ፕሮጀክት ቡድን አባላት ጋር የመገናኘት ዕድሉን አገኘች፡፡ ከከፍታ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የትምህርት ዕድልን ያላገኙ እና ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ወጣቶችን ማስተማር መኾኑ ደግሞ አጋጣሚው ጥሩ ኾነላት፡፡ መድኃኒትም ፕሮጀክቱን ተቀላቅላ ጉድለቴ ብላ ያመነችውን ማንበብና መጻፍ ያለመቻል ችግሯን ለመቅረፍ ‹‹የወጣቶች ማንበብና መጻፍ ፕሮግራም›› በተሰኘው መርኃ ግብር ውስጥ መማር ጀመረች። በዚህም የማንበብ ክህሎቷን አሳድጋ በ‹‹ደረጃ ሁለት›› ትምህርቷን ተከታትላ ማጠናቀቅ የቻለች ሲኾን፣ አካዳሚያዊ ውጤቷም ከምርጥ 12 ውጤቶች መካከል አንዱ ለመኾን በቅቷል።

መድኃኒት ከዚህ የማንበብ ክህሎት ሥልጠና በኋላ ደግሞ፣ አሁንም ከከፍታ ፕሮግራም፣ ለወጣቶች ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ የኾኑ ክህሎቶችን የሚያጎናጽፉ ተከታታይ የክህሎት ማዳበሪያ ሥልጠናዎች እንደሚሰጡ ሰማች፡፡ እነኚህ ክህሎቶች በዋናነት እርሷ ለነበረችበት ሁኔታ በእጅጉ አስፈላጊ ነበሩ፡፡ በተለይም በሥራ መስክ እንዴት ስኬታማ መኾን እንደሚቻል እና ሊደርሱ የሚችሉ ጥቃቶችንም እንዴት መከላከል እንደሚቻል፣ ከዛም አልፎ በሥነ-ተዋልዶ ጤና ዙርያ ተገቢ ግንዛቤ የሚሰጥ ነበር፡፡ እነዚህ ለወጣቶች የሚሰጡ የክህሎት ሥልጠናዎች፣ ወጣቶች በአካባቢያቸው ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲጓዙ፣ ከሌሎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በምን መልክ ቅርጽ ማስያዝ እንደሚችሉ፣ ትጉህ ሠራተኞች እንዲኾኑ እና ግባቸውን እንዲያሳኩ የሚያስችሉ የክህሎት፣ የባሕሪ እና የግል ስብዕና ለውጥ ፈጣሪ ሥልጠናዎች ናቸው።

እንዲህ ያሉ ልዩ ልዩ የውስጣዊ ክህሎት (soft skills) ሥልጠናዎች፣ መድኃኒት ከራሷ ኾነ ከሌሎች ጋር ውጤታማ በሆነ መንገድ ግንኙነት እንድታበጅ የሚያስችሏትን ክህሎቶች እና ስብዕናዊ ዐቅሞች ለግሰዋታል። እንዲህ ያሉ ሥልጠናዎች ወጣቶች ለሚኖራቸው ቀጣይ ስኬት መሠረት ከመጣል ጀምሮ፣ ከሌሎች ጋር ተግባብተው እና ተባብረው እንዲሰሩ፣ በተጨማሪም ከሰዎች ግላዊም ይኹን ሙያዊ ሁኔታዎች ጋር ተላምደው እንዲተጉ ያላቸው ጠቀሜታ ትልቅ በመኾኑ ሌሎች ወጣቶችም ተመሣሣይ ሥልጠና መውሰድ ይገባቸዋል የሚለውን ዕምነት ከፍ ያደርገዋል።

ከፍ ብለን ባነሳናቸው ሁኔታዎች ውስጥ አልፋ እዚህ የደረሰችው መድኃኒት፣ አሁን ላይ ወደፊት የሚኖራትን የተሻለ ሕይወት ተስፋ ከማድረግ አልፋ፣ ከሰራተኛነት ወደ ሥራ ፈጣሪነት አስተሳሰብ ተሸጋግራለች፡፡ አሁን ላይ የራሷን ሥራ ለመጀመር እንዴት ማቀድ እና መምራት እንዳለባት ተገቢውን ትምህርት ወስዳም በሙያዋ ራስ-በቅ ለመኾን መንገዱን ይዛለች። በጉዳዩ ዙርያ ከባለቤቷ ጋር ከተነጋገረች በኋላም የራሷን የቡና መሸጫ ንግድ ሥራ መሥራት ጀምራለች። አሁን ላይ በቀን ይኽንኑ ሥራዋን እያከናወነች፣ ማታ ደግሞ መደበኛ ትምህርቷን ለመቀጠል ወስናለች። የከፍታ ፕሮግራም አካል እንደመኾኗ መጠንም ትምህርቷን ትቀጥል ዘንድ አስፈላጊዎቿ ለትምህርት የሚኾኗት ቁሳቁሶች ድጋፍም ተበርክቶላታል።

መድኃኒት አሁን ላይ በሥራዋ ለመቀጠልም ኾነ የተለያዩ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶችን ለማሸነፍ ከሚችሉ የተማሩ ሴቶች ተርታ ለመሰለፍ ጥሩ ተስፋ አላት ብሎ መግለጽ ይቻላል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...