ከቴምር ፕሮፐርቲ መኖሪያ ቤት የሚገዙ ደንበኞች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ልዩ የሼባ ማይልስ ስጦታ ሊያገኙ ነው

Date:


  * ስምምነቱ ለቤት ፈላጊዎች ተጨማሪ ጠቀሜታን የያዘ ነው

ቴምር ፕሮፐርቲ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ .ም በሰጠዉ መግለጫ መሠረት መኖሪያ ቤት የሚገዙ ደንበኞች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ልዩ የሼባ ማይልስ ስጦታ የሚያገኙበት ዕድል ተዘጋጅቷል ብሏል።

የዜጎች የቤት ባለቤት መሆን ቅንጦት አለመሆኑን ማሳያ በሚሆን መልኩ በተመጣጣኝ ዋጋ ቤት ገንብቶ በማስረከብ ላለፉት አስር አመታት በታማኝነት የዘለቀው ቴምር ሪል ስቴት አሁን ደግሞ ለደንበኞቹ የተለየ ጠቀሜታ የሚያስገኝ ዕድልን ይፋ አድርጓል።

የቴምር ሪል ስቴት አስር የስኬት አመታት በዘርፉ በተለየ የማርኬቲንግ ስትራቴጂ፤ ስምና አመኔታን ያተረፈበት መሆኑን ደንበኞቹ እማኝ ሆነውታል።

ቤት ገንብቶ ግዙ ከማለት ይልቅ ቤት ፈላጊዎች የት እንዲገነባላቸው እንደሚፈልጉ በመጠየቅ የቤት ፈላጊዎችን ምኞት በማሳካት ለብዙዎች እፎይታን ሰጥቷል።

አሁን ደግሞ ደንበኞቹን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርግና በአይነቱ የተለየ “በቤትዎ አለምን ይዙሩ” የተሰኘ ስምምነትን የአፍሪካ ኩራት ከሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ለመፈፀም ተዘጋጅቷል።

ይሄውም፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ “ሸባ ማይልስ” በተሰኘው ተደጋጋሚ በረራ ለሚያደርጉ ደንበኞች የሚሰጠው ማበረታቻ ፕሮግራሙ አማካኝነት የሚሰጥ ተጨማሪ የጉዞና ተያያዥ ዕድሎች ተጠቃሚነትን የያዘ ስምምነት ነው።

በዚህ ስምምነት መሰረት የቴምር ሪል ስቴት ደንበኞች የሚገዙትን የቤት ወይም የሱቅ አይነት መሰረት ያደረገና የከፈሉትን መጠን ያማከለ የዓለም አቀፍ በረራ የማይልስ ዕድል የሚያገኙ ይሆናል።

የቴምር ደንበኞች በዚህ ስምምነት መነሻነት የሼባማይልስ ደረጃቸው እንደ ክፍያቸው ሁኔታ እያደገ የሚሄድ ሲሆን፤ ከብሉ ወደ ሲልቨር፣ ከሲልቨር ወደ ጎልድ ወይም ከብሉ ወደ ጎልድ የማሳደግ ዕድልንም ይሰጣል።

ደንበኞች በሚገዙት ቤት አልያም ሱቅ መሰረት ከ50% በታች ክፍያ ሲፈጽሙ በእያንዳንዱ 1 ዶላር ክፍያ 2.5 ማይልስ የሚያገኙበት ዕድል ይኖራቸዋል።

እንዲሁም 50% እና ከዚያ በላይ ክፍያ የሚፈጽሙ ደንበኞች በእያንዳንዱ 1 ዶላር ክፍያ 3.5 ማይልስ ሽልማት የሚያገኙበትን ዕድል ተመቻችቷል።

ይህ የአጋርነት ስምምነት በተለያዩ የአለም ክፍሎች ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቤት ገዥዎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታንም የሚያስገኝ ነው።

ቴምር ፕሮፐርቲ በዚህ የሽርክና ስምምነት በተለይም በውጭ ሀገራት የሚገኙ ደንበኞቹ የተጨማሪ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉ ለደንበኞቹ ያለውን ከበሬታ የሚያመላክት ነው።

ከዚህ ባለፈ፤
ቴምር ፕሮፐርቲ ዶሃ፣ ዱባይ፣ ሮም፣ በርሊን፣ ፓሪስ እና ዋሽንግተን ዲሲ ከተሞች በመዘዋወር ከደንበኞች ጋር የመቀራረብ ስራን የሰራ ሲሆን በቀጣይም በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልል ከተሞች፣ በአውሮፓና አሜሪካ መሰል እንቅስቃሴን ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን በድጋሚ መዝጋቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ

የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም መቆጣጠር...

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ20 አትሌቶች  የማስጠንቀቂያ አውጥቷል

በውድድሩ ላይ ያልተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይመለከታል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓለምአቀፍ...

የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር፤ ለወረራ የታለመ ማደናገሪያ? ሩሲያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች!

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ውጥረትን ለመቀነስ...