ከወደ ግብፅ የዛቻ ሪፖርቶች

Date:

“በህዳሴ ግድቡ ጉዳይ ኢትዮጵያን የማስፈረማችን ዕድል በማክተሙ፣ ግብፅ ራሷን የመከላከል መብቷን ልትጠቀም ነው..”
~የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ ባድር አብደላቲ

የግብፅ ሚዲያዎች በኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ GERD ዙሪያ እያዳረሱት የሚገኘው መረጃ፣ አዲስ አበባ አስገዳጅ ስምምነት እንድትፈርም ያደረገቻቸው የአመታት የተቀናጁ ጥረቶች ግብ ያልመታላት ካይሮ በአሁንዊ ሐሳቧ ያንፀባረቀችውን ዛቻ አዘል አረፍተነገር የሚያስተጋባ ነው።

     እናም ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት ያለ ካይሮ ይሁንታ የህዳሴ ግድቧን ገንብታ እና አጠናቅቃ ለማስመረቅ ዝግጅት መጀመሯ የድርድር ደጃፎችን በመዝጋቱ አገሪቱ “መብቴ” የምትለውን በተለይም የ”ሃይል አማራጭ ለማለት ፈልጋ ነው” በሚል በበርካቶች የሀገሪቱ ልሂቃን እየተብራራ የሚገኘውን “አማራጭ” የምትጠቀም ይሆናል ሲሉ እያስነበቡ ይገኛል።

ይሁንና ግብፃዊው የውጭ ጉዳይ ምኒስትር  አብደላቲ ከወርሃ ሰኔ መጨረሻ 2025 ወዲህ የሰጡት ጋዜጣዊ  መግለጫ ቢይኖርም፣ ከወቅታዊው የሰሜን ኢትዮጵያ ውጥረት አኳያ ግን ይህ በሀገሪቱ ብዙኃን መገናኛዎች እንዲሰራጭ የተደረገው መልዕክት በቸልታ መታየት የሌለበት ይመስላል።

eslemanabay የዓባይልጅ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...