‹‹ከፍታ የልጅነት ሕልሜን እንዳሳካ ፈር አስይዞኛል››

Date:

ገነት መኮንን

ገነት መኮንን ነዋሪነቷ በዲላ ከተማ ነው፡፡ የ23 ዓመቷ ገነት፣ ተገቢውን ዲሲፒሊን የተላበሰች ነርስ የመኾኑ ብርቱ መሻት ያላት ሴት ናት፡፡ ይኽንን ፍላጎቷን እውን ለማድረግ ደግሞ በወላጆቿ ድጋፍ በፓራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ ዲላ ቅርንጫፍ ለትምህርት ተመዘገበች። ገነት በትምህርቱ የነበራት ጉዞ እጅግ የሠመረ ነበር፡፡ ሕልሟን ለማሳካት ታደርግ በነበረው ብርቱ ትጋት ምክንያትም፣ በኮሌጁ ከነበሩ ጎበዝ ተማሪዎች መካከል አንዷ መኾን ችላለች። ገነት የልፋቷን ፍሬያማነት የሚያሳየው የኮሌጁን መውጫ ፈተና በብቃት ማለፏ ብቻ አልነበረም፡፡ ከዚያም አልፋ የፓራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅን ሜዳሊያ ጭምር ማጥለቅ በመቻሏም ጭምር እንጂ።

ገነት የኮሌጅ መመረቂያ ጊዜዋ ሲቃረብ ታዲያ፣ የከፍታ ፕሮጀክት የተቀናጀ የወጣቶች ኢንሼቲቭ ለማኅበረሰቡ በተለይም ደግሞ እንደርሷ ላሉ ወጣቶች ዐቅም ግንባታ የሚኾኑ ልዩ ልዩ የአገልግሎት ፓኬጆችን ማቅረቡን ሰማች። ገነት ዓላማዋ በዕውቅት ራሷን ማብቃት እና ሥራ ተቀጥሮ ራስን መቻል በመኾኑ፣ ከፍታ የሚሰጠውን የዐቅም ግንባታ ሥልጠና ለመውሰድ በእጅጉ ፈለገች። የአጋጣሚ ነገር ኾነና፣ በዲላ ከተማ ውስጥ በተለይም ለሥራ ፈላጊዎች በተዘጋጀው የዲጂታል ትምህርት ሥልጠና ፕሮግራም ላይ የመሳተፍ ዕድሉን አገኘች፡፡ ይህ ሥልጠና የተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮችን እንዴት ገቢ ወደሚያስገኝ ሥራ መቀየር እንደሚቻል አስፈላጊውን እውቀትና ክህሎት የሚያስታጥቅ ጠቃሚ መድረክ ኾኖ አገኘችው። ለከፍታ ፕሮጀክት ምሥጋና ይግባውና ያ ዕድል ማኅበራዊ ሚዲያን ለተማረችበት ሙያ የመጠቀም ብቃቷ በእጅጉ እንዲያድግ አግዟታል።

ይኽ ከኾነ በኋላ ባለው ጥቅምት ወር ደግሞ፣ ገነት ለከፍታ ዲላ ቅርንጫፍ ለወጣቶች የጤና አገልግሎት ሰጪ ኾና ለመቀጠር የሚያቃ ክፍት የሥራ መደብን ተመለከተች።

ገነት ባጋጠማት ዕድል ተደስታ፣ መሥፈርቶቹን በጥንቃቄ ገምግማ ለማመልከት ወሰነች። በዘርፉ የሥራ ልምድ ባይኖራትም የነበራት ቁርጠኝነት እና ቀናነት ታይቶ ለጽሑፍ እና ቃለ መጠይቅ ፈተና ከተመረጡት መካከል አንዷ ለመኾንም በቃች። ጠንክራ ሰራተኝነቷን እና ያላትን ዕምቅ ዐቅምም ለቀጣሪ ቡድኑ በማሳየት ማሳመን ቻለች፡፡ ቀጣሪዎቿም ሙያውን በሒደት እንደምታዳብረው በማሰብ በረዳት ሰራተኝነት እንድትሰራ ጠየቋት። ተስማማች፡፡

በአሁኑ ወቅት ገነት በሥራ ማመልከቻዋ ላይ እንዳስቀመጠችው ኃላፊነቷን በሙሉ ልብ እየተወጣች ትገኛች። በተለያዩ የሥነ ተዋልዶ ጤና/ቤተሰብ እቅድ ተግባራት ዙርያም ለወጣቶች ተስማሚ አገልግሎቶችን በንቃት በመሥጠት ላይ ትገኛለች፡፡ ከዚህም ባሻገር መረጃን በመቀያየር ተግባራት ላይ በትጋት ሥራዋን ከማከናወን ጀምሮ፣ በከፍታ ሥልጠናዎች፣ ስብሰባዎች እና ዐውደ ጥናቶች ላይ ንቁ ተሳታፊ ኾናለች። አሁንም ታዲያ የማይናወጥ ፍላጎቷ የተዋጣለት ነርስ መሆን ነው። ያም ኾኖ የአጭር ጊዜ እቅዷ፣ በተሰማራችበት መስክ የሙሉ ጊዜ የወጣቶች ጤና አገልግሎት መሥጠት ነው።

ለማጠቃለል ያህል፣ ገነት መኮንን ለከፍታ ፕሮጀክት እና ለአስደናቂ ሰራተኞቹ በተለያዩ የሕይወት ጉዞዎቿ ዘርፎች ላደረጉላት ድጋፍ እና ሥልጠና ልባዊ ምሥጋናዋን ታቀርባለች። በእነሱ ምክር እና በከፍታ ወጣቶች ፕሮጀክት በኩል በተሰጧት ዕድሎችም ምኞቷን ወደ ተጨባጭ ስኬት በመቀየር በመረጠችውና በምትወደው የነርስ ሙያ ራሷን ስኬታማ ለማድረግ የምትራመድበትን ፍኖት ዘርግታለች።

ግዮን መጽሔት ቅጽ 6 ቁጥር 220 ታህሳስ 12 2017 ዓ.ም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የህዳሴ ግድቡ ውዝግብ በፖለቲካዊ ሳይሆን በቴክኒካዊ መንገድ መፈታት አለበት

በአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ፣ እና የመካከለኛው ምስራቅ...

የ7 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ አለመከናወኑ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሚተዳደሩ 7 የጋራ መኖሪያ...

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ በ80 ዓመታቸው ከዚህ...