ከ430 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Date:


የ ጉምሩክ ኮሚሽን ከህዳር 19 እስከ ህዳር 25 ቀን 2018  ዓ.ም ባደረገው ክትትል ከ402 ሚሊዮን ብር  በላይ የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 28 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ ከ430 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን ገለፀ፡፡

ኮሚሽኑ በቁጥጥር ስር ከዋሉት የገቢ እና ወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አዳዲስ እና ልባሽ ጨርቅ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ተሽከርካሪ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የግንባታ እቃዎች፣ የመዋቢያ እቃ፣ ጫት፣ አደንዛዥ እፅ፣ መድኃኒት፣ ምግብ ነክ እቃ፣ ቡና፣ ማዕድናት እና የውጭ ሀገር ገንዘብ ይገኙበታል ሲል ገልጿል፡፡

ሞያሌ፣ አዋሽ እና ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ መያዛቸውን የገለፀው ኮሚሽኑ በቅደም ተከተላቸውም 103.7 ሚሊዮን፣ 84.4 ሚሊዮን እና 72.9 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ መቻላቸውን ጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በጥቆማ እና በበረራ የተያዙ መሆናቸውን ጠቅሶ የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 11 ተጠርጣሪዎች እና 14  ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከጥር 1 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ለጫት ላኪዎች የቅድመ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መስጠት ይቆማል

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከጫት ወጪ ንግድ ፈቃድና የብቃት...

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...