ታሪካዊው የማንችስተር ሲቲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬቨን ዴብሮይን ሀውልት ሊሰራለት እንደሆነ ይፋ ተደርጓል።
ማንችስተር ሲቲ ለኬቨን ዴብሮይን ሀውልት እንደሚያቆም በዛሬው ዕለት በይፋ አረጋግጧል።
የቤልጂየማዊው አማካይ ኬቨን ዴብሮይን ሀውልት ከኢትሀድ ስታዲየም ውጪ ላይ እንደሚገነባ ተገልጿል።
ስለ ሀውልቱ መገንባት አስተያየቱን የሰጠው ዴብሮይን “ ይህ ማለት ሁልጊዜም የዚህ ክለብ አካል እሆናለሁ ማለት ነው “ ሲል ተናግሯል።
አክሎም “ ወደፊት ከቤተሰቤ ጋር ወደዚህ ስመለስ ራሴን ማየት ስለምችል ሁልጊዜም እዚህ እሆናለሁ ” ብሏል።
ኬቨን ዴብሮይን በተጨማሪም በአካዳሚው በስሙ አንዱ መንገድ እንደተሰየመለት መዘገቡ ይታወሳል።
