ይህ ቀን በብዙዎች በጣም ሲጠበቅ ቆይታል፤በመጨረሻም የ40 ዓመቱ የዓለም እግር ኳስ ኮከብ ፖርቹጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከስምንት ዓመት ጣፋጭ የፍቅር ጓደኝነት በኃላ ከጆርጂና ሮድሪጌዝ ጋር የዓለማችን እጅግ በጣም ውዱን ጋብቻ መፈፀሙና ቀለበት ማሠራቸው ይፋ ሆኗል።
የሁለቱን ሙሽሮች በይፋ በትዳር መጠቃለላቸውንና ቀለበት ማሠራቸውን የሮናልዶ የረዥም ዓመት የፍቅር አጋር ሆና የቆየችው
ጆርጂና ሮድሪጌዝ የሁለቱን ፎቶና የጋብቻ ዳይመንድ ቀለበቷን በኢንስታግራም ገጿ ላይ በማጋራት አለም ሁሉ ይወቅልኝ ብላለች።
በ2017 የፍቅር ግንኙነት እንዳላቸው ይፋ ያደረጉት ሁለቱ ልጆች በስምንት ዓመት ቆይታቸው አምስት ልጆችን በጋራ አፍርተዋል።መንትዮቹ ሴቶች የ8 ዓመት ጥንዶች ኤቫ ማሪያ እና ማቲዎ፣የ7 ዓመትዊ አላና እና የ3 ዓመቷ ቤላና የ15 ዓመቱ ክርስቲያኖ ጁኒየርን በቀደም ግንኙነት በጋራ አፍርተው ቆይተዋል።
ከዚህ ውጪ ሁለቱ ጥንዶች በ2022 ከሶስት ዓመቷ ቤላ ጋር መንታ ሆኖ የተወለደው ኤንጅል ይህቺን አለም ለማየት ሳይታደል እንደተወለደ ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል።
የ40 ዓመቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶና የ31 ዓመቷ ጆርጂና ሮድሪጌዝ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቁት እሷ በምትሠራበት የጉቺ ብራንድ መደብር ውስጥ ሲሆን የፍቅር ግንኙነት አለን ብለው ወደ አደባባይ የወጡት ደግሞ በ2017 ነው።
ሁለቱ የዓለማችን ደስተኛና የተቀማጠለ ህይወትን የሚመሩ ጥንዶች በአሁን ሠዓት የሳውዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ አድርገው ቅንጡ ህይወት እየኖሩ ሲሆን በዲሴምበር 2022 አል-ናስርን ተቀላቅሎ በመጫወቱ በዓመት 177 ሚሊዮን ፖውንድ ወይም 238 ሚሊዮን ዶላር ወደ ካዝናው የሚከት የአለማችን ውዱ ተጫዋችና ቤተሠብም ለመሆን ችሏል።
✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)
