ዋሽንግተን ለቃችሁ ውጡ ትራምፕ

Date:

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ ቤት አልባ ሰዎች ከተማዋን በፍጥነት ለቀው እንዲወጡ አዘዙ።

ፕሬዝዳንቱ በትሩዝ ማህበራዊ ሚድያ ባሰፈሩት ጽሁፍ በዋና ከተማዋ የሚኖሩ ቤት የሌላቸው ሰዎች በአፋጣኝ እንዲወጡ ወይም እንዲባረሩ ነው ያሳሰቡት። ትራምፕ ቤት የሌላቸው ሰዎች የሚቆዩምባቸው ቦታዎችን እንሰጣቸዋለን ፣ ነገር ግን ከዋሽንግተን ራቅ ባለ አከባቢ ነው ሲሉም አስታውቀዋል።

የዋይት ሀውስ አስተዳደር በበኩሉ፣ ትራምፕ ቤት የሌላቸውን ሰዎች ከከተማው ለማባረር ምን አይነት ህጋዊ ስልጣን እንደሚጠቀሙ ግልጽ አላደረገም።

በተጨማሪም ትራምፕ ወንጀለኞችን ለማሰር የፌደራል መኮንኖችን ለመጠቀም ቃል የገቡ ሲሆን ይህም “የጥቃት ወንጀልን ለማስቆም” ያለመ እንደሆነ ገልጸዋል።

ትራምፕ በጥር ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በዋሽንግተን ዲሲ የነበረው የጥቃት ወንጀል መጠን በ30 ዓመታት ውስጥ ዝቅ እንዳለ መረጃዎች ያሳያሉ ።ትራምፕም የከተማዋ ደህንነት ለማረጋገጥና ጥቃትን ለመቀነስ ወንጀለኞችን ማሰር እንደሚጀምሩ ነው ያስታወቁት ።

የዶናልድ ትራምፕ አስተያየት ተከትሎ በዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት ዘንድ የተለያ ስሜትን ፈጥሯል ።

አንዳንድ የአካባቢው ባለስልጣናት የትራምፕን አስተያየት የተቹ ሲሆን ፣ ሌሎች ደግሞ ፕሬዝዳንቱ የከተማዋን ደህንነት ለማሻሻል ያላቸውን ፍላጎት የሚያሳይ እንደሆነ ገልጸዋል።

በዋሽንግተን ዲሲ የቤት እጦትን ለመከላከል የሚሰራው የኮሚኒቲ ሽርክና እንደገለጸው ወደ 800 የሚጠጉ ሰዎች በከተማዋ ጎዳናዎች እንደሚያድሩ አስታውቋል ።
ተጨማሪ 3,275 ሰዎች በዋሽንግተን የአደጋ ጊዜ መጠለያዎችን ሲጠቀሙ 1,065 ሰዎች በሽግግር መኖሪያ ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ የኮሚኒቲ ሽርክና መረጃ ያመላክታል ።

ዘገባው የዘጋረወዲያን ነው

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...