ደራሲ እና ተዋናይ ቴዎድሮስ ተሾመ ያዘጋገው ውብ አዲስ ተከታታይ ድራማ በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መተላለፍ ሊጀምር መሆኑ ተነግሯል።
ድራማውን አስመልክቶ በጋራ መግለጫ የሰጡት አቶ ካሳሁን ጎንፋ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ፣ አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ የቴዲ ስቱዲዮ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ እንዲሁም ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ እሸቱ ናቸው።
በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በቅርቡ መታየት የሚጀምረው ውብ አዲስ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ለ 25 ዓመታት ያህል ሲታሰብ የኖረና የበጀት፣ የአቅም እና የማስተላለፊያ ቻናል እስኪገጣጠሙ እንደተጠበቀ ተነግሯል።
ውብ አዲስ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ የፍቅር ታሪክ ያለው ሲሆን በከፍተኛ ልብ ሰቀላ የታጀበ ነው ተብሏል። ድራማው 90 በመቶ ከቤት ውጭ ቀረጻ የሚደረግበት ሲሆን በተመሳሳይም 90 በመቶ ቀረጻው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ይከናወናል።
አይን አዲስ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ቀረጻ ቀሪውን 10 በመቶ ከአዲስ አበባ ውጭ በሞሮኮ እና ጋና ሲከናወን በተመሳሳይ የሁለቱ ሀገራት የጥበብ ባለሙያዎች ወደ አዲስ አበባ መጥተው ይሳተፋሉ።
በተጨማሪም የቴሌቭዥን ቀረጻው ከመከናወኑ በፊት ለጀማሪ ተዋንያን እድል ለመስጠት የአክቲንግ ስልጠናና ውድድር ይካሄዳል ተብሏል።
