ዝግ የነበረውን የኩዌት የውጭ ሃገር የስራ ስምሪት ተጀመረ

Date:

ከዚህ ቀደም አስፈላጊ የሚባለውን ስልጠና አጠናቅቀውና በግላቸውም ቢሆን የስራ ስምሪቱን ያገኙ ወጣቶች መሄድ አልቻልንም ብለው እንደነበር ይታወሳል፡፡

በወቅቱ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኩዌት ጋር ምንም ዓይነት የስራ ውል የለኝም ስለዚህ የሰለጠነውን የሰው ኃይል አልክም በማለት መልስ ሰጥቶ ነበር፡፡

አሁን ኢትዮጵያ በህጋዊ መንገድ ያሰለጠነቻቸውንም ይሁን አግባብነት ያለው መረጃ በማቅረብ በግላቸው የሚመጡ ሰዎችን ለመላክ ዝግጅቷን ማጠናቀቋን ሰምተናል፡፡

ሁለቱ ሀገሮች የአለም አቀፍ ህግን መሰረት ባደረገ መልኩ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን፤ በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ፈቃድ መስጫ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሃምሳሉ ባሻ ነግረውናል፡፡

ሁለት ሀገራት ስምምነት ሲያደርጉ የስራ ስምሪቱ የሠራተኛውን መብት በጠበቀ መልኩ እና ደህንነቱን ያረጋገጠ መሆን እንዳለበት ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ያስገድዳሉ፡፡

የአሁኑ የኢትዮጵያና ኩዌት ያደረጉት ስምምነት የሰራተኛውን የስራ ሰዓት የሚያስከብር፣ የጤና ኢንሹራንስን የሚጠብቅ፣ ደህንነቱን የሚያረጋግጥና ሌሎችንም ያካተተ እንደሆነ ከሃላፊው ሰምተናል፡፡

በግላቸው ወደ ኩዌት ስራ ያገኙ ወጣቶች አስፈላጊውን ሟሟላታቸው ታይቶ እና ህጋዊ መሆናቸው ተረጋግጦ የስራና ክህሎት ሚኒስቴርን ፍቃድ እንደሚያገኙ ነግረውናል፡፡

ከሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...