የመድፈኞቹ 1900ኛ የፕሪሚየር ሊግ ድል

Date:

የማንችስተር ዩናይትድ በሽንፈት ውስጥ የታየ ተስፋ


“ማጥቃት
ላይ የተመሰረተ አጫዋዎት ጨዋታዎችን እንድታሸንፍ ያደርግሀል፡፡ መከላካል ግን ከዋንጫ ጋር ያገናኝሀል”የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሰር አሌከስ ፈርጉሰን የተናገሩት ነው፡፡

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ መርሀ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ 75ሺ ተመልካቾች በታደሙበት ኦልድ ትራፎርድ በአርሰናል1 ለ 0 ተሸንፏል፡፡

ምንም እንኳን ጨዋታው በትክክልም ውጤቱን የሚገልጽ ባይሆንም አመቱን በሽንፈት ጀምሯል፡፡

ኤሪክ ቴንሀን በመተካትማንችስተር የደረሱት ወጣቱ አሰልጣኝ ሩብን አሞሪም ባለፉት ዓመታት ምህዋሩ የጠፋበትን ክለብ ወደ ቀደመ ጥንካሬው ለመመለስ የቡድን ግንባታውን ለመጀመር ፍንጭ የሰጡበትን ምሽት አሳልፈዋል፡፡

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ያስፈረሟቸው የፊት መስመር ተጫዋቾች ከኳስ ጋርም ይሁንያላ ኳስ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለቀጣይ የቡድኑ ውጤት መመለስ ቁልፍ ተጫዋቾች እንደሚሆኑ ገና በመጀመርያው ጨዋታ አሳይተዋል፡፡

ማንችስተር ዩናይትድ በሜዳው ባደረገው ጨዋታ በሁሉም የጨዋታ መመዘኛዎች ከአርሰናል ተሸሎ አምሽቷል፡፡ በኳስ ቁጥጥሩም፣ የግብ ዕድሎችንምበመፍጠር፣ ኢላማቸውን የጠበቁ ሙካራዎችን በማድረግ ቀያይ ሰይጣናቱ ከመድፈኞቹ የተሸሉ ናቸው፡፡

ነገር ግን በእግር ኳስ እነዚህ ሁሉ ጉዳዮች ወደ ሚጨበጥ ውጤት እስካልተቀየሩ ድረስ ዋጋ አይኖራቸውም፡፡ በኦልድ ትራፎርድ የሆነም ይሄው ነው፡፡

በጨዋታው ባለሜዳዎቹ የተሸሉ ቢሆኑም አሁንም ማስተካካል ያለባቸው በርካታ ጉዳዮች መኖራቸው ግልጽ ነው፡፡ በዋናነትየጎደለውን ሚዛን ማስተካከል ይሆናል፡፡

የዩናይትድ የፊት መስመር ብዙ ተስፋ  የሚጣልበት  ቢሆንም አማካይ እና ተከላካይ ክፍሉ ግን የሚቀሩት በርካታ ስራዎች ይኖራሉ፡፡ ባለፈው አመት 10 የግብ ዕዳ ይዞ ያጠናቀቀው ክለቡ የመከላከልችግር እንደነበረበት የሚያሳይ ሲሆን  አሰልጣኙ  ከግብ  ጠባቂ ጀምሮ ቀዳዳዎችን መሙላት ካልቻሉ በዚህ አመት የአምናው ስላለመደገሙ ዋስትና አይኖርም፡፡

በአንድ ቡሩኖ ፈርናንዴዝ ላይ ጥገኛ የሆነውየአማካይ ክፍሉም ቢሆን ሌላ ሁነኛ ተጫዋች የሚፈልግ ነው፡፡

በሌላ በኩል ቀያይ ሰይጣናቱ የቆመ ኳሶችን መከላከል ላይ ከሁሉም የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ ከ2023/24 የውድድር ዓመት በኋላ የዩናይትድን ያክል የማዕዘን ግብ የተቆጠረበት ክለብ የለም፡፡ ትላንት ምሽትካላፊዮሪ ያስቆጠራትን ጨምሮ 23 ግቦች ተቆጥረውበታል፡፡

የ40 አመቱ አሰልጣኝ ሩብን አሞሪም ዩናትድን ከተረከቡ በኋላ ካደረጓቸው 28 የሊግ ጨዋታዎች  ያሸነፉት ሰባቱን ብቻ ሲሆን በ16ቱ ደግሞ ተሸንፈዋል፡፡ የዩናይትድን የጨዋታ ሚዛን ማስተካለል እና እንደ ተጋጣሚ ሆኖ ለመቅረብ መስራት እዲሁም ለኋለኛውን ክፍል መፍትሄ ማበጀት የአሰልጣኙ ትልቅ የቤት ስራምይሆናል፡፡

አርሰናል ባለፉት ሦስት ተከታታ ዓመታት 2ኛ ሆኖ ከማጠናቀቅ ያለፈ ትልቁን የሊግ ክብር ማሳካት ያቻለው አርሰናል ምንም እንኳንበተጋጣሚው ብዙ ብልጫ ቢወሰድበትም ወሳኙን ሦስት ነጥብ በማሳካት ጅማሮውን አሳምሯል፡፡

በአርሰናል የተጫዋችነት ዘመኑ በሊጉ ወደ ልድ ትራፎርድ አምርቶ አንደም ጨዋታ አሸንፎ የማያውቀው ሚካኤል አርቴታ በአሰልጣኝነት ግን ለ2ኛ ጊዜም ዩናይትድን በሜዳው እናደጋፊው ፊት ያሸነፈበትን ውጤት አስመዝግቧል፡ ነገር ግን ከሊጉ ዋንጫ ጋር ከተገናኝ ሁለት አስርት አመታትን ላስቆጠረው የሰሜን ለንደኑ ክለብ ይሄ በቂ አይደል፡፡

በተለይ ባለፉት 3 እና 4 አመታት የቡድን ግንባታ ላይ ያሳለፈው አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ የተሰጠውን በቂ ጊዜ ለመጠቀም የአርሰናልንየዋንጫ ረሀብ ማስታገስ የሚጠበቅበት ይመስላል፡፡

አርሰናል በሊጉ መክፈቻ ከሜዳው ውጭ ለዚያውም ከምንጊዜም ተቀናቃኙ ማንችስተር ዩናይትድ ሦስት ነጥብ ማግኝቱ እንደ አንድ ጥንካሬ የሚወሰድ ነው፡፡ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የቀድሞው የሊቨርፑል አማካይ ስቴቨን ጀራርድ በሰጠው ሃሳብ አርሰናል ጥሩባልሆነበት  ምሽት ዩናይትድን በሜዳው ማሸነፍ  መቻሉ ረጅም ርቀት እንደሚጓዝ ማሳያ ነው ብሏል፡፡

በዝውውሩ በሁሉም የጨዋታ ክፍል በንቃት ተሳትፎ ያደረገው አርሰናል ከግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ ጀምሮ የኋላ መስመሩ ጥንካሬ አሁንም አብሮት እንዳለ በሚገባ አሳይቷል፡፡ ለዚህ ደግሞ የትላንቱን ጨዋታ ብቻ መመለክለት በቂ ይሆናል፡፡ ለዚህም ይመስላል  የቀድሞው የዩናትድ አንጋፋው አሰልጣኝ ሰር አሌከስ ፈርጉሰን ጠንካራ ተከላካይስላው ቡድን ሲናገሩ መካላከል ከዋንጫ ጋር ያገናኛል የሚል ሃሳባቸውን የሰጡት፡፡ 

ባለፉት ሦስት የውድድር ዓመታት በሊጉ ዝቅተኛ ግብ ከተቆጠረባቸው ክለቦች ቀዳሚው አርሰናል የቆሙ ኳሶችን በመጠቀም የሚስተካከለው አልተገኝም፡፡ የቆሙ ኳሶች አሰልጣኙ ኒኮላስ ጆቨርን ከማንችስተር ሲቲ ካመጣ በኋላ የእንግሊዝ ክቦች ፈተና ሆኗል፡፡ከ2021/22  የውድድር ጊዜ ጀምሮ 71 የቆሙ ኳሶችን ከመረብ አሳርፏል፡፡

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በተከታታይ በመሳተፍ 100ኛ አመታቸው ላይ የሚገኙት መድፈኞቹ በአንድ ክፍለ ዘመን ጉዟቸው 1900ኛ ድላቸውን አሳክተዋል፡፡

መድፈኞቹ ምንም እንኳን ከቲያትር ኦፍ ድሪምስ ሦስት ነጥብ ቢያገኙም በቀጣይ ሊያስተካክሏቸው የሚገቡ ጉዳዮችስ የትኞቹይሆናሉ ?

ባለፉት አመታት ጥያቄ የሚነሳበት እና አሁንም መሻሻል ያልቻለው ማርቲኔሊን የሚካኤል አርቴት ያልተቀረፈ ችግር ሆኗል፡፡

ብራዚላዊው የመስመር ተጫዋች ሲከላከል ጥሩ ቢሆንም በቦታው ግን ግብ ማስቆጠርም ይሁን ለግብ የሚሆኑ ኳሶች ላይ በመሳተፍ የሚጠበቅበትንማደረግ አለመቻሉ የአርሰናልን ቡድን ጎደሎ እንዲሆን የሚያደርገው ነው፡፡

ሌላኛው ደግሞ በ64 ሚሊዮን ፓውንድ ኢምሬትስ የደረሰውን ቪክቶር ጊዮኬሩሽን ወደ ጨዋታ ማስገባት ይሆናል፡፡ ብዙ ለሚጠበቅበት የ27 አመቱ አጥቂ ከጀርባው የሚገኙ እንደ ኦዴጋርድ አይነት የፈጥራ አቅማቸው ክፍ ያሉ ተጫዋቾች የግብ ዕድሎችን እንዲፈጥሩ ነጻነቱንመስጥት አስፋለጊ ይሆናል፡፡

በደክለን ራይስ፣ ማርቲን ዙቢሜንዲ እና ማርቲን ኦዴጋርድ የሚመራውን የአማካይ ክፍል የኳስ ቁጥጥሩ ለይ ይበልጥ እንዲሰራ ተለዋዋወጭ በመሆን ለአጥቂዎች አደጋ  የሚፈጥሩ ኳሶችን እንዲያቀብል ማድረግ የስፔናዊው ታክቲሺያን ቀሪ የቤት ስራዎች ይሆናሉ፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...