የሚሳዔልና ድሮን ጥቃት በዩክሬን ላይ

Date:



ሩሲያ ከዚህ ቀደሙ በከፋ መጠን ግዙፍ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት በዩክሬን ላይ አደረሰች ፡፡

ሩሲያ 728 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮንስ ) እና 13 ሚሳዔሎችን ተጠቅማ በኪዬቭ ላይ ጥቃት ማድረሷ አነጋጋሪ ሆኗል ፡፡

አሜሪካ ለዩክሬን የጦር መሳሪ ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል በዶናልድ ትራምፕ በኩል ይፋ ከሆነ በኋላ ነው ታይቶ የማይታወቀው ጥቃት በኪዬቭ ለይ የተፈጸመባት፡፡

በአንድ ምሽት 741 የአየር ጥቃት ሞስኮ ፈጽማብናለች በሚል የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ከሰዋል ፡፡

የዩክሬን አየር ኃይል 711 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ማክሸፉን እንዲሁም ሰባት ሚሳዔሎችን መቶ መጣሉን አሳውቋል ፡፡

በአንድ ቀን ብቻ እጅጉን ግዙፍ የተባለው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ደርሶብናል ብለዋል ዘለንስኪ ፡፡

በኒፕሮ ፣ኪዬቭ፣ሱሚ እና ሌሎች ግዛቶች ውድመት መመዝገቡንም የዩክሬን ባለስልጣናት አሳውቀዋል ፡፡

ዘገባው የኤቢሲ ነውስ ነው፡፡

NBCEthiopia

ሆኖ_መ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...