የራፐር አሌክስ ንጉስ “ሂፓፕ በአገርኛ” አርብ ይለቀቃል

Date:

ሰባት ሚሊዮን ብር በላይ የፈጀው “የድሮ አራዳ” የተሰኘው ሂፓፕ በአገርኛ አልበም ሊለቀቅ ነው ተብሏል።

ይህ አልበም የተሰራው በራፐር አሌክስ ንጉስ ሲሆን፣ የተለያዩ ባለሞያዎች እንደተሳተፉበት ተነግሯል።

ዛሬ ድምጻዊውና ሌሎች ባለሞያዎች በተገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ የተሰጠ ሲሆን፣ አልበሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመት እንደፈጀ ለማወቅ ተችሏል።

በተጨማሪም፣ ከሰባት ሚሊዮን ብር በላይ የፈጀው ይኸው አልበም፣ ሙሉ በሙሉ በድምጻዊ አሌክስ ንጉስ ፕሮዲዩስ የተደረገ ስለመሆኑ ተገልጿል።

በዚሁ አልበም ላይ በግጥምና ዜማ ድምጻዊው አሌክስ ንጉስ፣ ሁንአንተ ሙሉ፣ ሃብቶም፣ ዲጄ ሴም ሲሳተፉ፣ በሙዚቃ ቅንብር ደግሞ ፓፓ ዌዋ እና ዲናር፣ እንዲሁም በሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ከአልበሙ 9 ሙዚቃዎች ፓፓ ዌዋ እና 1 ሙዚቃ ዲናር እንደተሳተፉበት ድምጻዊው ተናግሯል።

ከአልበሙ “ወይንዬ”፣ “ውብቂት” እና “ውዷ ባለቤት” የተሰኙ ሦስት የሙዚቃ ቪዲዮዎች ተሰርተው “ተጠናቅቀዋል” ተብሏል።

“የድሮ አራዳ” አልበም ስለ ፍቅር፣ ስለ አገር፣ ስለ ወጣቶች እና ስለ ስራ የሚያጠነጥኑ ዜማዎች እንደተካተቱበት ሲጠቀስ፣ ድምጻዊ አሌክስ ንጉስ ከዚህ ቀደም ወገቧን፣ “ኢትዮጵያ ትቅደም፣ ነይ ነይ፣ ለምን ብቻ ዕይታ” በሚሉት ዜማዎች ዕውቅናን አግኝቷል፡፡

“የድሮ አራዳ” አልበም የፊታችን አርብ ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም. በአሌክስ ንጉስ ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናልና በሁሉም ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች እንደሚለቀቅ ተጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ለሊት እንቅልፍ የለኝም

"አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ያሳስበኛል፤ እኔ አሁን 86 ዓመት...

አዎ ነበሩ ….

🔘የሁሉም አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሓጅ ዑመር🔘ነፍስዎ በሰላም ትረፍ "...

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ሳር ቅጠሉ የሚወዳቸው

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ሳር ቅጠሉ የሚወዳቸው የሀይማኖት...