የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ሳርኮዚ ከእስር መለቀቃቸዉ ተገለጸ

Date:

የፓሪስ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ሳርኮዚ ዛሬ ከእስር እንዲፈቱ እና በፍትህ ቁጥጥር ስር እንዲሆኑ ወስኗል፡፡

በ2007 ከሊቢያ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ሞክረዋል በሚል የአምስት ዓመት እስራት ከተፈረደባቸው ከሶስት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ነው ዉሳኔዉ የተሰጠዉ፡፡

የ70 አመቱን ሳርኮዚ ከፓሪስ ላ ሳንቴ እስር ቤት ይዘዉ የሚወጡ መኪኖችን መመልከቱን ፋይናንሻል ታይምስ ነዉ የዘገበዉ፡፡

ፍርድ ቤቱ የቀድሞዉ ፕሬዝዳንት ከፈረንሳይ ግዛት እንዳይወጡ እንዲሁም ከሌሎች ተከሳሾች እና ምስክሮች ጋር እንዳይገናኙ አግዷቸዋል፡፡

ሳርኮዚ ከተፈረደባቸዉ በኋላ በዘመናዊ የፈረንሳይ ታሪክ ውስጥ ወደ እስር ቤት የተላኩ የመጀመሪያው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሆነዋል።

የፈረንሳይ ህግ አደገኛ እንደሆኑ ለሚታሰቡ ወይም ወደ ሌላ ሀገር ይሸሻሉ ተብለዉ ለሚጠረጠሩ ሰዎች እና ማስረጃዎችን ለመጠበቅ ወይም በምስክሮች ላይ ጫና እንዳይፈጠር ለመከላከል እስር መኖር አለበት ሲል ይደነግጋል፡፡

ከ2007 እስከ 2012 ፈረንሳይን የመሩት ሳርኮዚ የተለያዩ ክሶች ቀርበዉባቸዋል ሲል ያስነበበዉ ፋይናንሻል ታይምስ ነዉ፡

ህዳር 01/2018 ዓ.ም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...