የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ግብአት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት በ2017 ዓ.ም በክፍለ ከተማና ትምህርት ቤቶች የ4ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ላይ ድጋፍና ክትትል ለሚያደርጉ ባለሙያዎች በተዘጋጀ ቼክሊስት ላይ ገለጻ አድርጓል፡፡
በኦረንቴሽኑ ለባለሙያዎች ገለጻ ያደረጉት የቢሮው የትምህርት ግብአት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክተር ወ/ሮ ምስራቅ ብርሃነመስቀል በድጋፍና ክትትሉ የሚገኙ ውጤቶችን መሰረት በማድረግ ፍረጃ የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመው በፍረጃው መሰረት የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩ አካላትን የምናበረታታ እጥረት ያለባቸውን ደግሞ አሰራራቸውን እንዲያስተካክሉ ድጋፍ የምናደርግበት ይሆናል ብለዋል ፡፡ ዳይሬክተሯ አያይዘውም ድጋፍና ክትትል የሚያደርጉ ባለሙያዎች የተዘጋጀውን ቼክሊስት መሰረት አድርገው በቂና ሙያዊ ስነምግባርን የተከተለ መረጃ እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡
በድጋፍና ክትትል ስራው የተማሪዎች ምገባ አገልግሎትና የከተማ ግብርና አረንጓዴ ስራዎች አፈጻጸም ላይ ትኩረት በማድረግ በ11ዱ ክፍለ ከተሞች እንዲሁም ትምህርት ቤቶች የሚካሄድ ሲሆን፤ የድጋፍና ክትትል ስራው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ባለሙዎች እንደሚደረግ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
