የአለም ባንክ የኢትዮጵያን የሪል ስቴት ዘርፍ በገንዘብ የመደገፍ ፍላጎት አለኝ አለ

Date:

በሌላ በኩል በሪል ስቴት አልሚዎች እና በቤት ገዥዎች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶች በድርድር መፍትሄ እንዲያገኙ የሚሰራ የግልግል ዳኝነት ቡድን እየተቋቋመ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

በኢትዮጵያ የሪል ስቴት ልማት ከተጀመረ 30 ዓመት ሆኖታል።

በእነዚህ ጊዜያት በርካታ ዜጎች የቤት ባለቤት መሆናቸው፤ የብዙዎች የአኗኗር ዘይቤም መቀየሩ ይጠቀሳል።

የዚያኑ ያህል ዘርፉ ላይ የሚነሱ ችግሮችም አሉ።

አንዱ በሪል ስቴት አልሚዎች የሚሰሩ ቤቶች አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች ታሳቢ ያደረጉ አይደሉም፤ ውድ ናቸው የሚል ነው።

የቤቶቹ ዋጋ እነዚህኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን በተለያዩ አጋጣሚዎች ጥያቄ ሲቀርብ ይሰማል።

ባለፈው ሚያዝያ ወር የተመሰረተው የኢትዮጵያ የሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር ግን የቤቶቹ ዋጋ ውድ ነው በሚለው ሃሳብ አይስማማም።

አቶ ከድር ሰይድ የማህበሩ ዋና ፀሃፊ ሲሆኑ አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች የሪል ስቴት ቤቶች ባለቤት እንዲሆኑ መፍትሄው በአነስተኛ ወለድ ፤ በረጅም ጊዜ የሚከፈል ብድር እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በሪል ስቴት አልሚዎች ላይ የሚቀርበው ሌላው ቅሬታ ባሉት ጊዜ እና የጥራት ደረጃ ቤቶችን ሰርተው አያስረክቡም የሚል ነው።

በዚሁ ምክንያት በአልሚውና እና በደንበኛው መካከል  አለመግባባቶች ሲፈጠሩ አንዳንዴም ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ሲያመራ ይታያል።

የተባሉት ችግሮች እንደሚገጥሙ የሚናገሩት ዋና ፀሃፊው አቶ ከድር – የግልግል ዳኝነት አይነት ስራ የሚሰራ ቡድን ማህበሩ እያቋቋመ እንደሚገኝ ነግረውናል።

ማህበሩ በቅርቡ ከአለም ባንክ ተወካዮች ጋር መወያየቱን የነገሩን አቶ ከድር በውይይቱ ባንኩ የኢትዮጵያን የሪል ስቴት ዘርፍ በገንዘብ መደገፍ እንደሚፈልግ ተረድተናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አሁን ላይ 57 አባላት እንዳሉት ሠምተናል።

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...