የአሜሪካ መንግሥት ለቀድሞዋ ም/ፕሬዚዳንት የሚያደርገውን ጥበቃ አቆመ

Date:

የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር “ሴክሬት ሰርቪስ” በተባለ ተቋም በኩል ለካማላ ሐሪስ የሚያደርገውን ጥበቃ ማቆሙን አስታወቀ፡፡

የቀድሞዋ ምክትል ፕሬዚዳንት በአሜሪካ መንግሥት የሚደረግላቸው ጥበቃ የሚያበቃው በሚቀጥለው ዓመት 2026 እንደነበር የዲደብሊው ዘገባ ያመለክታል፡፡

በሀገሪቱ ሕግ መሰረት፤ ከኃላፊነታቸው ከተሰናበቱ በኋላ ምክትል ፕሬዚዳንቶች ለስድስት ወራት፣ ፕሬዚዳንቶች ደግሞ ዕድሜ ልካቸውን ጥበቃ እንደሚደረግላቸው አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ይሁንና የቀድሞው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ከዋይት ሐውስ ከመሰናበታቸው በፊት በካማላ ሐሪስ ጥያቄ የአሜሪካ መንግሥት የሚያደርግላቸውን ጥበቃ ለተጨማሪ ስድስት ወራት አራዝመው እንደነበር ምንጮች ለአሶሼትድ ፕሬስ ተናግረዋል።

በመንግሥት የሚደረግላቸው ጥበቃ እንዲቆም የተደረገው ካማላ ሐሪስ “107 ቀናት” በሚል ርዕስ ያሳተሙትን የሕይወት ታሪካቸውን ለማስተዋወቅ በተዘጋጁበት ወቅት ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...