የአሜሪካ የኢሚግሬሽን ተቆጣጣሪዎች በከፊል ከሚኒሶታ ሊወጡ ነው

Date:

ከፍተኛ ተቃውሞ የተቀሰቀሰባቸው የአሜሪካ 700 ኢሚግሬሽን ተቆጣጣሪዎች ከሚኒሶታ በከፊል ለቅቀው እንደሚወጡ ተገለፀ።

ሕጋዊሰነድ የሌላቸውን ስደተኞች ከአሜሪካ በማባረር ጉዳይ የትራምፕ ቀኝ እጅግ ሆነው እያገለገሉየሚገኙት ቶም ሆማን የትራምፕ አስተዳደር በሚኒሶታ የሚገኙትን የኢሚግሬሽን ተቆጣጣሪዎች ቁጥርን ለመቀነስ  ከግዛቲቱ ባለሥልጣናት ጋር ከስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ እርምጃ መውሰዱን አስታውቀዋል።በታ

ታኅሣሥ ወር የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚኒሶታ የሚገኙ ሰነድ አልባስደተኞችን ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ለፌደራሉ የኢሚግሬሽን ኃላፊዎች ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር።

ይህንንም ተከትሎ ከ2000 በላይ የኢሚግሬሽን እና የጉሙሩክ ተቆጣጣሪዎች ከጥር ጀምሮ በሚኒሶታ ተሰማርተዋል።በዛሬው ዕለት ውሳኔው ይፋ ከመደረጉ በፊት የተወሰኑ የፌደራል ተቆጣጣሪዎች ሚኒሶታንለቅቀው መውጣታቸው የተገለፀ ሲሆን፣ በግዛቲቱ የሚቆዩት የተወሰኑ የኢሚግሬሽን እና የጉሙሩክ ሠራተኞች ብቻ ይሆናሉ ተብሏል።

የፌደራል የኢሚግሬሽን እና የጉሙሩክ ተቆጣጣሪዎች በሚኒሶታ ግዛት ውስጥ ሁለት ነጭ አሜሪካውያንን ተኩሰውከገደሉ በኋላ ከፍተኛ ቁጣ ተቀስቅሷል።የግዛቲቱ

ነዋሪዎች በተለያዩ አካባቢዎች ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተው ነበር። ይህንንምተከትሎ የሚኒሶታ አስተዳዳሪ ቲም ዋልዝ እና የሚኒስታ ከንቲባ ጃኮብ ፍሬይ የፌደራል የኢሚግሬሽን ተቆጣጣሪዎች ከግዛቲቱ ዋና ዋናአካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ለቅቀው እንዲወጡ ጠይቀዋል።ትራምፕ ግን አስተዳደራቸው ነገሮችን “ትንሽ እንደሚያረግብ” ተናግረው ነበር።ሆማን በዛሬው ውሳኔያቸው የፌደራል መንግሥቱ ተቆጣጣሪዎች ቁጥር ከታኅሣሥ በፊት ወደነበረበትመመለሱን ተናግረዋል።ነገር ግን ተ

ጨማሪ ተቆጣጣሪዎችን ለማስወጣት የአካባቢው ሕግ አስከባሪዎች እና የሰፊውማኅበረሰብ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...