የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሶስት የጦር መርከቦች ወደ ደቡብ አሜሪካዋ ሀገር ቬንዝዌላ እንዲጓዙ ማዘዛቸው ተመላከተ።
ፕሬዝዳንቱ በቬንዝዌላ ያለውን ከፍተኛ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ለመግታት በማለም ይህንን ውሳኔ መወሰናቸውም ተገልጿል።
አሜሪካ የቬንዝዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮን በአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር የምትከሳቸው ሲሆን መሪውን ለመያዝ ለሚያግዛት እሰጣለሁ ያለችውን በዕጥፍ አሳድጋ 50 ሚሊዮን ዶላር ማድረጓ ይታወሳል።
ሶስቱ የአሜሪካ የጦር መርከቦች 4 ሺህ 500 የአሜሪካ ወታደሮችን ይዘው ወደ ቬንዝዌላ ዳርቻ እየተጓዙ መሆኑንና በሚመጣው እሁድ እንደሚደርሱ ስማቸው ያልተጠቀሰ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ባለስልጣናት መግለፃቸውን ሮይተርስና ኤኤፍፒ ዘግበዋል።
የጦር መርከቦቹ ጉዞ በቬንዝዌላ ያሉ የአደንዛዥ ዕፅ ቡድኖች በአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ስጋትነት ላይ ምላሽ ለመስጠት ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።
የቬንዝዌላው ፕሬዝዳንት ማዱሮ ለአሜሪካ ስጋት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሚሊሻዎችን በበሀገሪቱ እንደሚያሰማሩ አስታውቀዋል።
