የአረብ ሊግ ዋና ፀሐፊ  ለእስራኤል  ጥቃት“ቆራጥ እርምጃ” መውሰድ ያስፈልጋል አሉ

Date:

“ወንጀለኛውን የእስራኤል የጦርነት ማሽን አስቁሙ”‘

የአረብ ሊግ ዋና ፀሐፊ አሕመድ አቡል ጌት፣ በዶሃ በተካሄደው የአረብና የሙስሊም ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ቀጥተኛ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርበዋል።

“ወንጀለኛውን የእስራኤል ወታደራዊ ማሽን ከዚህ አሳፋሪ ጦርነት ማስቆም ላይ ሁላችንም ትኩረት ማድረግ አለብን” ብለዋል።

እስራኤል በኳታር ለፈፀመችው የአየር ጥቃት  “ቆራጥ እርምጃ” መውሰድ እንደሚያስፈልግና ከኳታር መንግሥት ጋር “የአረብ-እስላማዊ ትብብርን” ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን  አጽንኦት ሰጥተዋል ሲል  ስፑኒክ አስነብቧል።

ይህ መግለጫ እስራኤል አሜሪካ ባቀረበችው የሰላም ሐሳብ ላይ ለመወያየት በዶሃ ተሰብስበው በነበሩ የሃማስ መሪዎች ላይ ዘመቻ “የአሳት ጉባኤ” በሚል ጥቃት ከሰነዘረች በኋላ የመጣ ነው። እስራኤል ለጥቃቱ ኃላፊነት ብትወስድም፣ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው “ያልታሰበ አደጋ” ሲሉ ገልፀውታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...