የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

Date:

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች ከደን ጭፍጨፋ ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መሆን እንዳለበት አስቀምጧል።

ኢትዮጵያዊያን አነስተኛ ገበሬዎች  ቡና የተመረተበትን ትክክለኛ የመሬት መገኛ የሳተላይት መረጃ  እንዲያቀርቡም ያስገድዳል።

የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን የዳይሬክተር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሰፊሳ አባቡ እንደገለፁት፥ባለፉት ሁለት አመታት ህጉ ያስቀመጣቸዉን መስፈርቶች ለሟሟላት እየተሰራ መቆየቱን አንስተዋል።

መስፈርቱን በቴክኖሎጂ ለማረጋገጥ ሲባልም የአርሶ አደሮች ማሳ በጂፒኤስ እና በዘመናዊ የዲጂታል ካርታ መረጃዎች እንዲደገፍ ማድረግ ስራ ላይ ቆይተናል ብለዋል ኃላፊዉ።

34 መቶ የሆነዉ የቡና ገበያ መዳረሻዉ በአዉሮፓ መሆኑን ተከትሎ ገዥዎችን ከሚወክሉ አካላት ጋር የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ዉይይት ማድረጉን ገልፀዋል።

ሆኖም ህጉ የሚኖረውን ተፅዕኖ ለመቀነስ ሌሎች ከአዉሮፓ ዉጪ ያሉ መዳረሻዎች እየተፈለጉ መሆኑን ኃላፊዉ ነግረዉናል።

ቻይንና ጨምሮ ሌሎች መዳረሻ ሀገራት የሚገዙት የቡና መጠን ጭማሪ እያሳየ ነዉ የሚሉት አቶ ሰፊሳ፥የቡና መሸጥ አቅም እንዲያድግ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ መስፈርቱን ማሟላት ካልቻለች ከ4 መቶ 53 ሚሊየን ዶላር  የሚደርስ የቡና ወጭ ንግድ ገቢ ሊታጣ እንደሚችል ይገመታል።

በ2025 መጨረሻ ተግባራዊ እንዲሆን ታቅዶ የነበረዉ ህጉ የአውሮፓ ፓርላማ የትግበራ ጊዜውን በአንድ ዓመት ማራዘሙ ይታወሳል።

በዚህም ለትላልቅ ላኪዎች እስከ ታህሳስ 2026፣ ለአነስተኛ ላኪዎች እስከ ሰኔ 2027 ድረስ መስፈርቱን አሟልተው እንዲገኙ ጊዜ ገደብ ተሰጥቷል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...