ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በአሜሪካ እና በፈረንሳይ በብዙ ሚሊዮን ዶላር ቅጣት ከተጣለበት በኋላ በሳምንት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ በአውሮፓ ህብረት ተቀጥቷል።
የአውሮፓ ህብረት በጎግል ላይ 2.95 ቢሊዮን ዩሮ (3.45 ቢሊዮን ዶላር) ቅጣት የጣለ ሲሆን ይህም ጎግል በአስር አመታት ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ መቀጣቱን ያሳያል፡፡
የአውሮፓ ኮሚሽን በ27ቱ ሀገራት ጎግልን ከአውሮፓ አታሚዎች ምክር ቤት የቀረበለትን ቅሬታ ከመረመረ በኋላ በቴክኖሎጂው ውስጥ ያለውን ፉክክር እያዛባ ነው ሲል ከሷል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በጎግል ላይ ለተጣለው ቅጣት ውሳኔውን በመተቸት ለአውሮፓ ህብረት ምላሽ የሰጡ ሲሆን በህብረቱ ላይ ሰፊ የንግድ ምርመራ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።
ጎግል የአውሮፓ ህብረት ውሳኔን በመተቸት በፍርድ ቤት እንደሚቃወም አስታውቋል።
