የአፍሪካ ህብረት የአሜሪካ የጉዞ እገዳ አሉታዊ ተፅእኖ እንዳያሳድር ጠየቀ

Date:

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የ12 ሃገራት ዜጎች ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ የሚያግደው መመሪያ ላይ ትናንት መፈረማቸው ተዘግቧል።

አዲሱ መመሪያ የሚመለከታቸው የአፍጋኒስታን ፣ ምያንማር፣ ቻድ ፣ ኮንጎ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኤርትራ ሄይቲ ኢራን ሊቢያ ሶማሊያ ሱዳንና የየመን ዜጎች ናቸው።

ከዚህ ሌላ የብሩንዲ የኩባ ላኦስ ሴራልዮን ቶጎ ቱርክሜንስታን እና ቬንዝዌላ ዜጎች ደግሞ ከፊል እገዳ ተጥሎባቸዋል።

ይህንን ተከትሉም የአፍሪካ ህብረት “ሚዛናዊ፣ በማስረጃ ላይ የተመሰረተ እና ለረጅም ጊዜ የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት አንፀባራቂ” የጉዞ እገዳ ፖሊሲ እንድትወስድ ሃሙስ እለት ጠይቋል።

ማንኛውም ሀገር የድንበር ጥበቃ እና የጸጥታ ሉዓላዊ መብት እንዳለው ያስገነዘበው የአፍሪካ ህብረት ፤ በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣ በትምህርት ልውውጥ፣ በንግድ እና በሰፊው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ “ለአስርተ አመታት በጥንቃቄ ተጠብቁ በቁየው ግንኙነት ላይ ” “አሉታዊ ተጽእኖ” እንዳያሳድር እንዳሳሰበው ገልጿል።

ህብረቱ በመግለጫው ሰላምን፣ ብልጽግናን እና ዓለም አቀፋዊ ትብብርን በማሳደግ ረገድ የአፍሪካ እና የአሜሪካን የጋራ ጥቅሞች አጉልቷል።

የአፍሪካ ህብረት “በአክብሮት” የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ከጉዞ እገዳው ውሳኔ በስተጀርባ ያለውን ማንኛውንም ችግር ለመፍታት “ግልጽ ግንኙነት እና አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ የትብብር ጥረቶች” ከሚመለከታቸው አገሮች ጋር “ገንቢ ውይይት ማድረግ” እንዲታሰብበት ጠይቋል ሲል አናዶሉ ዘግቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...