የአፕል የትምህርት መተግበሪያ ውድድርን ያሸነፈው ትውልደ ኢትዮጵያዊ

Date:

በዮርክ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ ዓመት የኮምፒውተር ምህንድስና ተማሪ የሆነው ናሆም ወርቁ ውስን የኢንተርኔት አገልግሎት ያላቸውን ተማሪዎች ለመደገፍ በተዘጋጀው”Access Ed” በተሰኘው የትምህርት መተግበሪያ ዓለም አቀፍ እውቅናን አትርፏል።

የተማሪ ናሆም ወርቁ የፈጠራ ሥራ በቅርቡ የተከበረውን የአፕል ስዊፍት ተማሪዎች
ፈተናን በማሸነፍ በዓለም ዙሪያ መተግበሪያውን ለአፕል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቡድን በካሊፎርኒያ አፕል ፓርክ እንዲያቀርቡ ከተጋበዙ11 ተማሪዎች መካከል አንዱ አድርጎታል።

በዝግጅቱ ላይም ከአፕል ኩባንያ ሃላፊ ቲም ኩክ ጋር የተገናኘ ሲሆን የፈጠራ
ስራውን አብራርቷል።

ተማሪው ከCP 24 ጋር በነበረው ቆይታ በልጅነቱ በትውልድ አካባቢው የኢንተርኔትእጥረት በተደጋጋሚ ሲያጋጥመው እንደነበር ጠቅሶ፥ ለዚህ ችግር የኢንተርኔት እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎችን ችግር ለመቅረፍ ፈጠራው ከኢንተርኔት ውጭ /ከመስመር ውጭ/ የመማሪያ መሳሪያዎችን ለማቅረብ ‘አክሰስ ኢድ’ የተሰኘውን መተግበሪያ መፍጠሩን ጠቅሷል።

ተማሪ ናሆም ወደ ቴክኖሎጂ ጉዞ የጀመረው የኮሮና ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅትእራሱን በተለያዩ አማራጮች በኮዲንግ በማብቃት እንደሆነ ይናገራል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...