የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የምክር ቤቱን 41ኛ መደበኛ ስብሰባ ባካሄደበት ወቅት፣ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት አዋጅን መርምሮ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።
የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) አዋጁ የዜጎችን ደህንነት፣ ብቃትና ተወዳዳሪነት ማጎልበት የሚያስችል ነው ብለዋል።
አክለውምን ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ዜጎች በሕጋዊ መንገድ ተጠቃሚ ያደርጋል ነው ያሉት፡፡
ምክር ቤቱ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1389/2017 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል ።
