በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ያሉ የቅርብ ጊዜ ክንውኖች፦
🔸 በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ የሚገኘው የኻን ዩኒስ ምስራቃዊ ክፍል ትናትና ጠዋት በእስራኤል የአየር ጥቃት እንደተፈፀመበት የፍልስጤም መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
🔸 ሁኔታው አስቸኳይ ቢሆንም እስራኤል የመድኃኒትና የሕክምና አቅርቦቶችን እንዲገባ መከልከሏን ቀጥላለች ሲሉ የጋዛ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ገልፀዋል።
🔸 የአል-ሺፋ ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር ሙሐመድ አቡ ሰልሚያ እንደተናገሩት፤፣ ሁለት ሺህ ሕፃናትን ጨምሮ ወደ አምስት ሺህ የሚጠጉ እጅና እግራቸውን ያጡ ሰዎች አፋጣኝ የሰው ሠራሽ አካላት ሕክምና ያስፈልጋቸዋል።
🔸 የማዘጋጃ ቤቱ ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው፣ ወደ 260 ሺህ ቶን የሚጠጋ ፍርስራሽ (ቆሻሻ) በጋዛ ጎዳናዎች እና የቆሻሻ መጣያ ቦታዎች ላይ ተከምሯል።
🔸 የአካባቢው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ የመስከረም 30 የተኩስ አቁም ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ በእስራኤል የጥቃት እርምጃ በጋዛ ሰርጥ ውስጥ 226 ሰዎች ተገድለው 594 ቆስለዋል።
🔸 ቅዳሜ ዕለት የሐማስ የፖለቲካ ቢሮ አባላት ኢስታንቡል ውስጥ ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳንን የተገናኙ ሲሆን፣ በጋዛ የተኩስ አቁም ሁኔታ እና አስቸኳይ ሰብአዊ ፍላጎቶች ላይ ተወያይተዋል።
