የእስራዔል ጦር ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ ወደ ጋዛ ታመራ የነበረን አነስተኛ ጀልባ መያዙን አስታወቀ።
ጦሩ የእርዳታ እህል ጭና ወደ ጋዛ ሰርጥ ስታመራ የነበረችን ጀልባ እና በውስጧ የነበሩ “የፍልስጤም ደጋፊ” ማህበረሰብ አንቂዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ነው የገለጸው።
ጀልባዋ በሰሜናዊ ጋዛ ወደ ምትገኘው የወደብ ከተማ አሽዶድ እያቀናች እንደነበርሬውተርስ አስነብቧል።
በወቅቱ እስራዔል ለጋዛ ሰብአዊ ድጋፍ እንዳይቀርብ የጣለችውን ክልከላ በመጣስ ወሳኝ ሰብአዊ ድጋፎችን ጭና ትጓዝ እንደነበርም ዘገባው አመላክቷል።
የእስራዔል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ጀልባዋ በሰላም በእስራዔል ባህር ዳርቻመድረሷን እና በውስጧ የነበሩ ሰዎችም ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ገልጿል።
እስራዔል ለታጣቂው ሐማስ መሳሪያ እንዳይቀርብለት በሚል ወደ ጋዛ ምንም አይነት
እርዳታ እንዳይገባ ክልከላ ጥላ ብትቆይም ባለፈው ሳምንት የተወሰነ እርዳታ የጫኑ ከባድ መኪናዎች ጋዛ ደርሰዋል።
@Arada_Fm
