የኦዲት ጉድለት በታየባቸው ተቋማት ላይ ተጠያቂነት ለማስፈን እንደሚሠራ ተገለጸ

Date:

በኦዲት ግኝቶች የሚታዩባቸው ተቋማት ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን በትኩረት እንደሚሠራ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ።

ቋሚ ኮሚቴው ህዳር 7 ቀን 2019 ዓ.ም. ከፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት አመራሮች ጋር የትውውቅ መድረክ ያካሄደ ሲሆን፣ የተቋሙን የሥራ እንቅስቃሴም በአካል ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶክተር አብርሃም አለማየሁ እንደገለጹት፣ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሀገርና የመንግሥት ሀብት ለታለመለት ዓላማ መዋሉንና ሕዝቡም ተጠቃሚ መሆኑን ለማረጋገጥ፣ የኦዲት ግኝት በሚታይባቸው ተቋማት ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን በትኩረት ይሠራል።

ሰብሳቢው በተጨማሪም ባለድርሻ አካላትና ኦዲት የሚደረግባቸው ተቋማት ስለ ኦዲት ምንነትና አስፈላጊነት ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ የሥልጠና መርሐ ግብሮች መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሠረት ዳምጤ በበኩላቸው፣ ባለፉት ዓመታት በተካሄዱ የኦዲት ምርመራዎች ምክንያት የዘጠኝ ተቋማት አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰዱንና ለ69 አመራሮችና ባለሙያዎች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መሰጠቱን ገልጸዋል።

በኦዲት ግኝቶች የሚታዩባቸው ተቋማት ላይ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የቋሚ ኮሚቴውን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ትብብር ወሳኝ መሆኑንም ዋና ኦዲተሯ አመልክተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞዛምቢክ አቻው ጋር ዛሬ ያደረገውን ወሳኝ ጨዋታ 1ለ0 ተሸነፈ !

በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ...

በአዲስ አበባ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የንባብ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

የንባብ ባህልን ለማነቃቃት ያለመ 15ኛው ከተማ አቀፍ የንባብ ፌስቲቫል...

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የኤንሪኮ ማቴይ ሽልማት ተሸለሙ

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በአፍሪካና በአውሮፓ መካከል ያለውን...