የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

Date:

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና የኪነ-ጥበብ ሕይወቱ ማጠቃለያ የሆነውን 26ኛ አዲስ የሙዚቃ አልበሙን ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ተደረገ።

ላለፉት ስድስት አሰርት ዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያኖረው አርቲስቱ፤ ይህንን አልበም ያዘጋጀው የቀደሙትን የሀገር ውስጥ የሙዚቃ ቅርሶች ሳይበረዙና ሳይለወጡ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ በማሰብ እንደሆነ ገልጿል።

አልበሙ 13 ትራኮችን የያዘ ሲሆን ዘመናዊ የሙዚቃ መሣሪያዎችን ከባህላዊ የቅኝት ድምፆች ጋር ያዋሐደ ፤ ይዘቱም ትውልድን፣ ፍቅርን፣ ሀገርን፣ የሕይወት ፍልስፍናን እና ማኅበራዊ እሴቶችን የሚያንጸባርቁ ግጥሞችን አካቷል።

በርካታ ወጣትና አንጋፋ የሙዚቃ አቀናባሪዎች የተሳተፉበት የጋሽ መሐሙድ የመጨረሻ አልበም  ሲሆን፤ አዲሱ ትውልድ የሀገሩን ባህልና ማንነት ሳይለቅ በዘመናዊነቱ እንዲቀጥልበት ጥሪ አቅርቧል።

ይሳቃል ኢንተርቴይመንት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅና ለማሰራጨት ኃላፊነቱን የወሰደው ይህ አልበም፤ በቅርቡ በSpotify፣ Apple Music፣ YouTube እና በሌሎችም ዲጂታል መድረኮች ላይ ለሕዝብ ክፍት የሚሆን ሲሆን፣ ከአልበሙ የተመረጠ አንድ ነጠላ ዜማ ለአዲስ ዓመት ዋዜማ ለአድማጮች እንደሚለቀቅ ታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ እና የቻይና አየር መንገዶች የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቻይና ሳውዘርን አየር መንገድ በቻይና...

ሁቲዎች በሳዑዲ የነዳጅ ኩባንያ አስተዳደር ሕንጻ ላይ በፈጸሙት ጥቃት በእሳት ተያያዘ

የሳዑዲ አረቢያ የኢነርጂ ሚኒስቴር በአገሪቱ ምሥራቃዊ ግዛት የሚገኘው ከዓለም...

የሹመት ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  ሹመት የሰጧቸው አመራሮች፡- 1. አቶ...

እንደዚህ ዓይነቱ ብልሹ ኣሰራርን ካላረምን በቀር መልካም ኣስተዳደርን …

በኣጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኣጠቃላይ...