ሰሜን ኮሪያ ባለፈው ሳምንት በሙከራ ላይ የነበረ የጦር መርከብ መፈንዳቱን ተከትሎ ሶስት ከፍተኛ ባለስልጣናትን አሰረች፡፡
የሀገሪቱ ማዕከላዊ ወታደራዊ ኮሚሽን እንዳስታወቀው ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ አደጋውን እንደተከላከለ ነው ፡፡
የፒዮንግያንግ ባለስልጣናት ሶስቱን ሰዎች በቁጥጥር ስር ካደረጉ በኋላ ተጨማሪ ምርምራ እያደረጉ መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
ባለስልጣናቱ የአደጋውን መንስኤ ባይነገሩም ሶስቱን ባለስልጣናት ተጠያቂ አድርገዋቸዋል ተብሏል፡፡
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጁንግ ኡን በሰጡት መግለጫ ክስተቱ የወንጀል ድርጊት (criminal act) ፍጹም ግዴለሽነት የታየበት እና ሀላፊነት የጎደለው ሲሉ ተችተውታል፡፡
