የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

Date:

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት ላይ ተጥለው የነበሩ የቪዛ እገዳዎችን በጊዜያዊነት ማንሳቱን አስታወቀ።

ይህም ማለት ዲቪ ደርሷቸው የነበሩ አመልካቾች ሰነዶቻቸውን ማቅረብ እና የተመደበላቸውን ኢንተርቪው መከታተል ይችላሉ ማለት ነው።

በአሜሪካ የዲቪ ሎተሪ እጣ የወጣላቸው ከ3ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከ53 ሺህ በላይ አፍሪካውያን የፍርድ ቤት እፎይታ ማግኘታቸው ተሰምቷል።

በዚህም ከኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ጋና እና 46 ከሚሆኑ የአፍሪካ ሀገራት የተመረጡ 53,939 ዕድለኞች የማመልከት ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወስኗል።

እንደ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ ከነዚህ መካከል 3,287 ያህሉ ኢትዮጵያውያን አመልካቾች ናቸው ብሏል።

አመልካቾች ኢንተርቪው መከታተል የሚችሉ ቢሆንም የ2026 በጀት ዓመት ከማበቃቱ በፊት እስከ መስከረም 20 ድረስ ቪዛ ካላገኙ ዕድሉ ሊያልፋቸው እንደሚችል ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...