የጃፓን ሾቶ ካራቴ ፌዴሬሽን ኢትዮጵያ ሻምፒዮና ተጠናቀቀ

Date:


ከነሀሴ 16/2017 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የጃፓን ሾቶ ካራቴ ፌዴሬሽን ኢትዮጵያ ሻምፒዮና ተጠናቀቀ። ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜ በተካሄደው መላው ኢትዮጵያ የጄኪኤስ ሻምፒዮና ከ330 በላይ ተወዳዳሪዎች ተሳተፈውበት በኦሮሚያ ክልል ተወካዩ ሻምፒዮን ካራቴ ክለብ አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቋል።

ለተከታታይ ሶስት ቀናት በአ/አ የተካሄደው ሻምፒዮና በኢትዮጵያ የካራቴ ስፖርት ታሪክ የአካል ጉዳተኛ ስፖርተኞች ጭምር ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉበት ነው።

በሻምፒዮናው የመዝጊያ መረሃ ግብር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንት ወርቅነህ ደመቀ የካራቴ ስፖርት የትውልድን መልካም ስብዕና በመገንባት አወንታዊ ሚና እንዳለው ገልፀው እንደዚህ አይነት ውድድሮችን ማስፋት እና ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።

የጃፓን ካራቴ ሾቶ ፌዴሬሽን ኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሰለሞን ዘውዱ በበኩላቸው ለ4ኛ ጊዜ የተደረገው ሻምፒዮና በብዙ ውጣ ውረዶች ውስጥ የተደረገ ቢሆንም አገርን በተለያዩ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ውድድሮች መወከል የሚችሉ ተተኪ ስፖርተኞች የታዩበት መሆኑን ገልፀዋል።

የጄኪኤስ ኢትዮጵያ ፌዴሬሽን በየዓመቱ እያካሄደ ያለው ሻምፒዮና እራሳቸውን ካልባሌ ቦታ እንዲጠብቁ ከማድረጉ በተጨማሪ ተወዳዳሪ እና ተፎካካሪ እያደረጋቸው መሆኑን የሻምፒዮናው ተሳታፊ ስፖርተኞች ተናግረዋል።

በውድድሩ ከአንድ እስከ ሶስት ላጠናቀቁ ተወዳዳሪዎች ከሜዳሊያ በተጨማሪ እንደየደረጃቸው የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በሻምፒዮናው የአካል ጉዳተኞችን ጨምሮ በርካታ ተወዳዳሪዎችን ያሳተፈው የአፋር ክልል ተወካዩ ብላክ ታይገር ካራቴ ክለብ የሻምፒዮናው ልዩ ተሸላሚ ሆኗል።

NBC Ethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...