የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን እንደሚለቁ አስታወቁ

Date:

የሊበራል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኤልዲፒ) አባላት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ቅሬታ ተከትሎ የጃፓንጠቅላይ ሚኒስትር ኢሺባ ስልጣናቸውን እንደሚለቁ አስታወቁ።

የ11 ወራት የስልጣን ዘመናቸውን ያጠናቀቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ሺገሩ ኢሺባ፣ ፓርቲያቸው በምርጫ ጥሩ አፈጻጸም ባለማሳየቱ ኃላፊነት እንዲወስዱ የሊበራል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኤልዲፒ) ውስጥ እየጨመረ የመጣውን ግፊት ተከትሎ ዛሬ  ስልጣናቸውን እንደሚለቁ አስታውቀዋል ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ኢሺባ “ብሔራዊ ቀውስ” ሲሉ የገለጹት ከአሜሪካ ጋር በተደረገው የታሪፍ ድርድር ላይ ዓርብ ዕለት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ እንደወሰኑ ተናግረዋል።


ኢሺባ “ሁሌም የምወስነው ተገቢው ጊዜ ሲደርስ ነው ስል ነበር። ከአሜሪካ ጋር የነበረው የታሪፍ ድርድር የተወሰነ ምዕራፍ ላይ የደረሰ በመሆኑ፣ አሁን ተገቢው ጊዜ ነው ብዬ አምናለሁ” ብለዋል። “ለቀጣዩ ትውልድ ቦታ ለመልቀቅ ወሰንኩ” ሲሉም አክለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...