የአፍጋኒስታኑ ታሊባን አሜሪካ ያቀረበችውን የጦር ሰፈር መመለስ ሀሳብ እንደማይቀበለው በድጋሜ አስታወቀ።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ የጦር ሰፈርን ለማስመለስ እየተደራደርን ነው የሚል ሀሳብ ቢሰጡም ታሊባን እንዲህ ዓይነቱ ተግባር ስምምነትን ይጥሳል በሚል ውድቅ አድርጎታል።
የባግራም አየር ሀይል የጦር ሰፈርን ለዋሽንግተን ታሊባን ይመልሳል የሚሉ መረጃዎች ከአሜሪካ በኩል መውጣታቸው አይዘነጋም።
እንዲህ ዓይነቱ የአሜሪካ ፍላጎት የ2020ውን የታሊባንና ዋሽንግተን ስምምነትን ያፍርሳል ተብሏል።
ጦሩ እንዲወጣ ስምምነት ነበረን አሁን እንዲመለስ የሚደረግበት ምክንያት የለም ሲል የካቡል አስተዳደር ግልጽ አድርጓል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት አፍጋኒስታን ባግራምን ካልመለሰች መጥፎ ነገር ይከሰታል ማለታቸውም ይታወሳል።
የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ሀሳብ ቻይናም የተቃወመችው ሲሆን ቀጠናዊ አለመረጋጋትን ዳግም ሊያመጣ ይችላል ተብሏል ።
ዘገባው የአር ቲ ነው።
