የፕሮቴስታንት ሙሉ ቸርች ኦርቶዶክስን ተቀበለ !

Date:



‎ኦርቶዶክስ ቀጥተኛዋ መንገድ ናት! /Hope Church Halifax/

‎በእንግሊዝ ሀገር የሚገኝና የፕሮቴስታንት እምነት አካል የሆነ Hope Church Halifax የተባለ ቤተክርስትያን ከነ-ተከታዮቹ ጠቅልሎ ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን መቀበሉ የድንግል ማርያምና የፃድቃንን አማላጅነት እንደሚቀበል ይፋ አድርጓል ።

‎ቤተእምነቱ hopehalifax.org/orthodoxy በድህረ ገፁ በኩል እንዳሳወቀዉ ከሆነ ለአምስት ዓመታት ሁሉ ስለ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሲያጠና እንደነበርና አሁን በይፋ የአንፆኪያ ኦርቶዶክስ (ግሪክ) ቤተክርስቲያንን መሰረተ እምነት መቀበሉን አውጇል።

‎በዚህ አቋሙም አንዳንዶች ሊገረሙ እንደሚችሉ ሲጠቅስ እውነታውን ግን ብርሃንን በምልዓት ወደ ማየት ተሸጋግረናልና ኑና እኛ የቀመስነውን እውነት ቀምሳችሁ እዩ በማለት ለሌሎችም ጥሪውን አቅርቧል። አያይዞም:- ውይይት የሚፈልግን ማንኛውንም አካል:- አቅራቢያው ወደሚገኙ የኦርቶዶክስ አጥቢያዎች ሄደው እንዲማሩ እንዲሁም የእነርሱን መርሃ-ግብራት እንዲለታተሉ ጋብዟል። በረጅም ጊዜ በጥንቃቄ መጻሕፍትን መርምረን ያገኘነውን ብርሃን ኑና እዩ ብሎ ጥሪ አቅርቧል።

‎ምንጭ hopehalifax.org/orthodoxy

‎የኔታ ቲዩብ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...