የፖለቲካ ጥያቄዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ጠንካራ የፌደራል ተቋማት እና ሕግ ያስፈልጋል

Date:


በሀገሪቱ የተፈጠሩና እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶች አንዱ ምክንያት ብዝኃነትን ለመቀበል ዝግጁ አለመሆን እና ከብዝኃነት ጋር አብሮ ለመኖር የሚያስችል ስርዓት ማበጀት አለመቻሉ፤ ለፌዴራል ስርዐቱ ገቢራዊነት አሁንም ችግር ሆኖ መቀጠሉን የሕገ መንግሥትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ለአሐዱ አስታውቋል።

የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ኃይለየሱስ ታዬ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙሃንነት የለም ብሎ መቀበል አይቻልም፤ በሀገሪቱ አሁን ያለው ትልቁ ችግር ብዝሃነትን ለመቀበል ዝግጁ አለመሆን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

‎ሕብረ ብሔራዊ የፌደራል ስርዓትን ለመተግበር ብዙ ቅድመ ሁኔታዎች አሉ፤ በዚህም የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት በሂደት ማሟላትና መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል።

‎የአስተምህሮ ማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አክለውም “ፌደራሊዝም ብሔርተኝነትን ማለዘብ አለበት” ያሉት ሲሆን፤ ፌደራሊዝምና ብሔርተኝነት አንድ ላይ የሚሄዱት ሁሉንም ብሔር አካታች የሆነ ሕብረ ብሔራዊ ስርዓት ሲኖር ብቻ ነው በማለት ገልጸዋል።

‎ሕብረ ብሔራዊ የፌደራል ስርዓትን ለመገንባት፣ ለማስቀጠል እንዲሁም ጫፍ የወጣ ብሔርተኝነትን ለማርገብ የሚቻለው፤ የሌሎችን ማንነት በመቀበል የአካታችነት ስርዓት ሲፈጠርና ሲረጋገጥ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

‎”ዋናው እና ትልቁ ጉዳይ ብዙሃንነትን ተቀብሎ ማስተዳደር ይሁን እንጂ ብሔርተኝነት የሚለውን አስተሳሰብ የምናብራራበት መንገድ በራሱ መስተካከል አለበት፤ ብሔርተኝነት ማለት ዘረኝነት ማለት አይደለም” ሲሉም ኃይለየሱስ ታዬ (ዶ/ር) አብራርተዋል።

አክለውም፤ ብዝሃነትን ለማስተዳደር የፖለቲካ ጥያቄዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ጠንካራ የፌደራል ተቋማት ያስፈልጋል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

“እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ብዙ ብሔር ባለባት ሀገር ውስጥ በብዝሃነት ዙሪያ በስፋት ከመስራት አንፃር ክፍተት አለ” ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ጥቂት የፌደራል ተቋማት ቢኖሩም በሚፈለገው ደረጃ እየሰሩ አለመሆኑን አንስተዋል።

‎”ብሔርተኝነት የውድድር ጉዳይ መሆን የለበትም፤ በመነጋገር ፤ በመወያየት እና በልዩነት ውስጥ በጋራ የመኖር አስተሳሰብ ሊሆን ይገባል፤ ለዚህም ጠንካራ የፌደራል ተቋማት ያስፈልጋል” ሲሉም ገልጸዋል።

‎”በሀገሪቱ ያለውን የፖለቲካ ባህል ማስተካከል ካልተቻለ ብዝሃነትን ማስቀጠልና ማረጋገጥ አይቻልም፤ ብሽሽቅ ከበዛበት አካሄድ መውጣት ያስፈልጋል” በማለት የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ኃይለየሱስ ታዬ (ዶ/ር) አሳስበዋል።

(አሐዱ ሬዲዮ) ‎

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...