የፖርቱጋል እና የስፔን አሠልጣኞች ስለማታው የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ምን አሉ?

Date:


ዛሬ ማታ 4 ሰዓት ፖርቹጋል ከ ስፔን በሚያደርጉት የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ዙሪያ የፖርቹጋሉ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ እና የስፔኑ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፉዌንቴ መግለጫ ሰተዋል።

በዚህም አሠልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ለፍፃሜው ጨዋታ ዕቅድ እንዳላቸው እና በዕቅዱም መሠረት ከ11ዱ ስብስብ ውጪ ያሉት እያንዳንዱ ተጫዋቾች አስፈላጊ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አሠልጣኙ በፍፁም ጥንቃቄ መጫወት እንዳለባቸው በማንሣት፣ በተለይም በመልሶ ማጥቃት ከዓለም ምርጥ በሆኑት በስፔኖች ላይ ምላሽ የሚሰጡበት መንገድ ፍፁም መሆን አንዳለበት አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ሮቤርቶ ማርቲኔዝ እንደገለጹት “ስፔን ኳሱን የሚቆጣጠሩ እና በፍጥነት የሚያጠቁ ተጫዋቾች አሏቸው፤ ነገር ግን ለፖርቹጋል አሸናፊነት ቁልፍ የሆነው ባለን ጠንካራ ነገር ላይ ፍፁም መሆን እና በነገሮች መቀያየር ሐሳባችንን አለመቀየር ነው” ሲሉ አክለዋል።

የስፔኑ አሠልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፉዌንቴ በበኩላቸው፣ ውድድሩን በቅርብ ጊዜ ከታዩት በጣም አስቸጋሪ ውድድሮች አንዱ መሆኑን ገልጹው፣ በመድረኩ ለየት ያለ የጨዋታ ጥራት እንደታየበትም አንሥተዋል።

አሠልጣኙ እንደተናገሩት “በአውሮፓ ውስጥ ካሉት 5 ምርጥ ብሔራዊ ቡድኖች 4ቱ የግማሽ ፍፃሜው ጨዋታዎች ውስጥ የነበሩ ናቸው፤ እየተነጋገርን ያለነው ስለ 3 የዓለም ዋንጫ አሸናፊዎች እና ስለ አውሮፓ ሻምፒዮን ነው” በማለት ስለውድድሩ ክብደት ገልጸዋል።

ሉዊስ ዴ ላ ፉዌንቴ አክለውም፣ ልጆቼ ሁኔታዎችን ማሸነፍ ይችላሉ፤ ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ ዳኛው የመጨረሻውን ፊሽካ እስኪነፋ ድረስ አንድ ዓይነት ሐሳብ፣ የቁርጠኝነት መንፈስ እና ጉልበት ይዘው ይጫወታሉ” ብለዋል ።

ታዲያ የማታው ጨዋታ የሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች አሠልጣኞች ጥልቅ ተሰጥኦ እና የአመራር ጥበብ የሚታይበት እንደሚሆን ይጠበቃል።

በሴራን ታደሰ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከጥር 1 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ለጫት ላኪዎች የቅድመ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መስጠት ይቆማል

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከጫት ወጪ ንግድ ፈቃድና የብቃት...

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...