“ነፃነት ባሕል እና ዘመናዊውን በማጣመር ኃይለኛ ድምፅ እና ደማቅ የመድረክ አቀራረብን በሥራዎቿ አሳይታለች፡፡ ዘፈኖቿ፣ ዜማና ግጥሞቿ በዘመናዊ ቃና የኢትዮጵያን ሕዝቦች ያንፀባርቃሉ” ሲል አወዳዳሪው በመግለጫው አስታውቋል፡፡
ድምፃዊቷ ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ አድናቆትን አትርፋለች። ነፃነት በሙያዊ ብቃቷ እና ለኢትዮጵያ ሙዚቃ እድገት ላበረከተችው አስተዋፅዖ ሶስት ታላላቅ ሽልማቶችን እንዳገኘች የውድድሩ አዘጋጅ የቴሌግራም ቻናል ገልጿል።
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የ2025 “ኢንተርቪዥን” ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ውድድር በሞስኮ እና በሞስኮ ክልል እንዲካሄድ አውጀዋል። ውድድሩ መስከረም 10፣ 2018 ዓ.ም በሞስኮ ይካሄዳል።
