ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፌደራል ሪዘርቭ ገዥዋን ከስልጣን አነሱ

Date:


ትራምፕ የፌደራል ሪዘርቭ ገዥ የሆኑትን ሊዛ ኩክን ከስልጣን እንዲነሱ ትዕዛዝ መስጠታቸውን አስታውቀዋል።

ትራምፕ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ኩክ፣ በአሜሪካ ሕገ-መንግስት እና በ1913ቱ የፌደራል ሪዘርቭ ሕግ መሰረት ከተሰጣቸው ስልጣን “ከአሁኑ ጀምሮ” ከስልጣን እንደተነሱ ገልጸዋል።

ትራምፕ የሪዘርቭ ገዢዋን ከብድር ማጭበርበር ክሶች ጋር ተያይዞ ከስልጣናቸው ለማባረር መወሰናቸውን ተናግረዋል ።

ይህ በዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ባንክ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ በመሆኑ፣ የባንኩን ነጻነት በተመለከተ ከፍተኛ ስጋት አሳድሯል።

ትራምፕ ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ የፌዴራል የሞርጌጅ ተቆጣጣሪ ያቀረባቸውን ክሶች በመጥቀስ፣ “በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ የሞርጌጅ ስምምነቶች ላይ የሀሰት መግለጫ ሰጥተዋል ብሎ ለማመን በቂ ምክንያት አለ” ብለዋል።

ትራምፕ በራሳቸው የማህበራዊ ትስስር ገጽ ‘ትሩዝ ሶሻል’ ላይ ባጋሩት ጽሁፍ “የፌዴራል ሪዘርቭ የወለድ ምጣኔን እና የመጠባበቂያና አባል ባንኮችን የመቆጣጠር እጅግ ትልቅ ሃላፊነት አለበት” ብለዋል።

ምንም እንኳን ትራምፕ ሊዛ ኩክን ከስልጣን የማንሳት ስልጣን እንዳላቸው ቢናገሩም፣ የፌደራል ሪዘርቭ ሕግ አንድ ፕሬዝዳንት ገዥን ከስልጣን ሊያነሱ የሚችሉት “በተገቢ ምክንያት” ብቻ እንደሆነ ይደነግጋል።

የዶናልድ ትራምፕ ውሳኔ ተከትሎ ኩክም ሆነ የፌዴራል ሪዘርቭ ምንም አይነት አስተያየት አልሰጡም።

ዘገባው የቢቢሲ እና አልጄዚራ ነው

NBCEthiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...