የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአካሄደው የገበያ ዳሰሳ ጥናት የቁጥጥር መስፈርቱን ያላሟሉ የተለያዩ የምግብ ምርቶች ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ያሳስባል፡፡
የኢትዮጵያ ምግብ መድኃኒት ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣንና ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጋር በመቀናጀት በአደረገው የገበያ ጥናት በተለያዩ አካባቢዎች ተመርተው በገበያ ውስጥ አስገዳጅ የደረጃ ምልክት ሳይኖራቸዉ ወይም ሳይለጥፉ እንዲሁም አስገዳጅ የገላጭ ፅሁፍ ስታናድርድ CES 73 ሳያሞሉ ወደ ገበያ መውጣታቸውን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
መስፈርቱን ያላሟሉት የምግብ ምርቶች የገበታ ጨው፣ የለውዝ (የኦቾሎ) ቅቤ፣ የምግብ ዘይት፣ አቼቶ፣ ከረሜላ እና ማር ሲሆኑ በምርቶቹ ላይ የተገኘው ጉድለት ደግሞ የማምረት የብቃት ማረጋገጫ (ሲኦሲ) የሌላቸው፣ የአምራች ድርጅት ስምና አድራሻ እንዲሁም አስገዳጅ የደረጃ ምልክት የሌላቸው፣ ምርቱ የተመረተበትና የሚያበቃበት በተለይም መለያ ቁጥር የሌለውና የምርቱ ጥሬ ግብዓት ዝርዝር ያለመገለፅ ናቸው፡፡
በዚህም መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት የምግብ ምርቶች ጥራትና ደህንነታቸው ያልተረጋገጠ በመሆኑ ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ባለሰልጣን መስሪያቤቱ ያሳስባል፡፡
የገበታ #ጨው
- ሴፍ 16. ዜድ
- ማሚ 17. ማሂ
- ሶም 18. ኤልሳ
- ኒያ 19. አርኪ
- ኤ ኤም 20. ሜናታ
- አሜን 21. ፎር ኤፍ
- ኑና 22. ዋን
- ዘመን 23. አዮዲን
- ስኬት 24. ዳግም
- ቴንሲያ 25. ቶም
- እሙ 26. ጆይ
- ጠሊል 27. ሳሊህ
- መስቱራ 28. ዛክ
- ጊዜ 29. ትዝታ
- ኩል 30. ዊን
የለውዝ (ኦቾሎኒ) ቅቤ
- መና 8. ዓለም
- ፋና 9. ፀዬ (Tseyie)
- ሰናይት 10. አዱሊስ
- MAZA( ኤም ኤ ዜድ ኤ) 11. ጊፍት
- ሉሲ 12. ስዊት
- ኤ ኤፍ 13. ሐበሻ
- አያልነህ 14. ሀናን
የምግብ ዘይት
- ፍትህ 7.ዝናሽ
- የኛ 8. ፍፁም
- Tina Oil 9. ሙሐ
- ፋሚሊ 10. ተስኒም
- እድገት 11. ፀሐይ
- ረዲ 12. እፎይታ
አቼቶ
- Hade Aceto
ከረሜላ
- Hawi Fruits candy
- Best Jar
- MAMIE
- Mamie Lollipop
- Best Pop Lollipop ማር
- ፀደይ ማር
- ኬሪ የጫካ ማር
(የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን)
