ፕሬዚዳንት ዊሊያም የጤና ክፍያ መክፈል ለማይችሉ 1.5 ሚሊየን ኬንያውያን መንግስት የይከፍላል

Date:

መንግስት ይህንን ክፍያ መክፈል ያልቻሉ 1.5 ሚሊየን ዜጎችን መለየቱን እና የሁሉንም ክፍያ መንግስት እንደሚሸፍን ተገልጿል።

የማህበራዊ ጤና አስተዳደር በኬንያ ከዚህ በፊት የነበረውን የብሔራዊ ሆስፒታሎች ፈንድ እንዲተካ የተደረገ ተቋም ሲሆን በዚህ ተቋም የተመዘገቡ ዜጎች ነፃ የህክምና አገልግሎትንም እንዲያገኙ ያስችላል።

በኬንያ የጤና ኢንሹራንስ ፕሮግራም ውስጥ ለመግባት ሰዎች በአመት 3600 የኬንያ ሽልንግ መክፈል ይጠበቅባቸዋል ሲባል መክፈል ያልቻሉትን ወጪ ለመሸፈን መክፈል ከሚችሉ ኬንያውያን ከገቢያቸው 2.75 በመቶ የማህበራዊ ጤና አስተዳደር መዋጮ ይሰበሰባል።

ዊሊያም ሩቶ በኬንያ የሚገኙ ከደረጃ 1-4 ያሉ ሆስፒታሎች የማኅበራዊ ጤና አስተዳደር ምዝገባ ላደረጉ ዜጎች ነፃ ህክምና እንዲሰጡ ማዘዛቸውም ይታወሳል።

ሩቶ በእነዚህ የጤና ማዕከላት ክፍያ እንዲከፍሉ የተደረጉ ሰዎችም በስልክ ጥሪ ማዕከል ጥቆማ እንዲሰጡ ብለው ነበር።

ፕሬዚዳንቱ ከመጠን በላይ ያስከፍላሉ ያሏቸውን ሆስፒታሎች መዝጋታቸውን አንስተው ሆስፒታሎቹ ነፃ አገልግሎት እንዲሰጡ መንግስት አስፈላጊውን ክፍያ መፈፀሙን አንስተው ተናግረዋል።

ኬንያ ዜጎቿ ሙሉ ለሙሉ የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ እየሰራች እንደምትገኝ ስትገልጽ እስካሁንም ከ25.8 ሚሊየን በላይ ኬንያውያን የማኅበራዊ ጤና አስተዳደር ምዝገባ አድርገዋል ተብሏል።

Source: Kenyan

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...