ዶክተር ላጲሶ ጌታሁን ድሌቦ (ላጲሶ ጌ. ድሌቦ) የታሪክ ምሁር ና ተመራማሪ ሲሆኑ የእስልምና እምነት ተከታይ ከነበሩት ከሀዲያ እና ከንባታ ወላጆች ነው የተወለዱት።
አስራ አንድ አመት ሲሆናቸው እናትና አባታቸው በሞት ሲለዩዋቸው በአሜሪካን ሚስዮኖች አማካኝነት ትምህርታቸውን መከታተል ጀመሩ።
ላጲሶ የሚለው ስም እናትና አባታቸው ያወጡላቸው ስም ቢሆ ንም በዘመኑ ሲደረግ እንደነበረው ወደ ትምህርት ቤት ሲገቡ ስማቸው ተቀይሮ ጌታሁን ድሌቦ እንደተባለ እና ይህ ስማቸ ው የዶክትሬት ትምህርታቸውን ጨርሰው ወደ ሐገራቸው እስከ ተመለሱበት ጊዜ ድረስ በዚሁ ጌታሁን ድሌቦ በሚለው ስም ይጠሩ እንደነበር ይናገራሉ።
ከዶክትሬት ትምህርታቸው በሇ ላ ግን የስራ ቅጥራቸው ላይ ወላጆቻቸው ያወጡላቸውን ስም እና ስርዓቱ የሰጣቸውን ስም አጣምረው ላጲሶ ጌታሁን ድሌቦ ተብለው እንዲጠሩ እንዳደረጉ ኢቢኤሥ (EBS) ላይ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ ተናግረዋል፡፡ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አሜሪካን ሐገር በአሜሪካን ሚስዮኖች ተልከው በታሪክ ዘርፍ እስከ ዶክትሬት ድግሪ
ተምረዋል። ከዶክትሬት ማእረጋቸውም በሇላ የ’ጵሮፌሰርነት ማእረግ ተሰቷቸው ለሁለት አመታት ቨርጂኒያ ዩንየን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሲያስተምሩ ቆይተው አብዮቱ ሲፈነዳ የታሪክ አካል መሆን አለብኝ በማለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።ያኔ የነበራቸውን ስሜት ሲገልፁ የኢትዮጵያ አንድነትን እንደ ጣኦት እያመለኩት መጣሁ ይላሉ።
ወደሀገራቸውም ተመልሰው በዚሁ ስሜትና ሀሳብ ዙሪያም ምርምራቸውንና ማስተማሩን እንደቀጠሉ ይናገራሉ።ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌታሁን ድሌቦ ብዙ የታሪክ መፃህፍትን ያሳተሙም ሲሆን አበይት በሆኑ ሀገራዊ የታሪክ ክስተቶችም ላይ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ማለትም በሬዲዮና በቴለቪ ዝን ላይ በመቅረብ ጠለቅ ያለ ትንተና በመስጠ ት ይታወቃሉ ።
ካሳተሟቸውም የታሪክ ስራዎች የሚከተሉት ይገኙባቸዋል።
- አጭር የጌዴኦ ህዝብ ታሪክ ከ1982-1966
- የቀይ ባህርና የአባይ ሸለቆ ሚና በኢትዮጵያ ታሪክ
- የምርትና የባህል ዘመቻ በከንባታና ሀዲያ አውራጃ
- የአዲስ አበባ መዲና እድገትና ሚና በኢትዮጵያ ታሪክ
- የኢትዮጵያ ረጅም የህዝብና የመንግስት ታሪክ
- የኢትዮጵያ የገባር ስርዓትና ጅምር ካፒታሊዝም 19ዐዐ- 1960
- የኢትዮጵያ የመከራ ስርዓትና የኤርትራ ጥያቄ
- ብሄራዊ ስሜት ብቻውን የታሪክ ምሁር አያደርግም – እ ፎይታ መፅሄት
- ኢትዮጵያዊነት ትላንትና ዛሬ – እፎይታ መፅሄት
- በአንዳንዶቹ የምርምር ስራዎች ላይ ፈጥነው ወደ ድምዳሜ የሚደርሱ እና ስሜታዊነትንም የሚያንፀባርቁ ሃሳቦችን አካተዋል በሚል ትችት ሲሰነዘርባቸው ይስተዋላል።
►ምንጭ
1.አርአያ ሰብ፣ ቃለ ምልልስ (EBS)
2.ታሪካዊ መዝገበ ሰብ (ጌታሁን እንግዳ)
