1 ሺህ 500 ሴቶች በየዓመቱ የሚያስጠልለው ማኅበር የቤት ኪራይ ፈተና ሆነበት

Date:

በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በሐዋሳ፣ በደሴ፣ በኮምቦልቻ እና በደብረ ብርሃን ከተሞች በየዓመቱ 1 ሺህ 500 ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች የሚያስጠልለው የሴቶች መጠለያና ልማት ማህበር፣ የአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎቹ የኪራይ መሆናቸው እንደፈተነው አስታውቋል።

የማኅበሩ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ማሪያም ሙኒር፣ “አብዛኛዎቹ የማኅበሩ ማዕከላት በኪራይ ቢሆንም በአንዳንድ አካባቢዎች የራሱን ቦታ አግኝቷል” ብለዋል።

ማኅበሩ በቅርብ ዘመዶቻቸው ወይም በሌሎች ግለሰቦች ፆታዊ ጥቃት ደርሶባቸው ጎዳና የወጡ ሴቶችን በመቀበል ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚሰጥም አብራርተዋል።

ወደ ማኅበሩ የሚገቡት አብዛኛዎቹ ተጎጂዎች ወጣቶች መሆናቸውን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሯ፣ ጥቃቱ ከደረሰባቸው በኋላ ተገቢውን የህክምና እርዳታ አለማግኘታቸው ችግሩን የበለጠ እንደሚያወሳስበው አስረድተዋል።

ማህበሩ ተጎጂዎች የህክምና አገልግሎት አግኝተው ስነ-ልቦናቸው እንዲጠነክር እንዲሁም፤ እንደ ልብስ ስፌት፣ ቤት አያያዝ፣ ፀጉር ስራ እና ሌሎች ሙያዎች ሰልጥነው የራሳቸውን ስራ እንዲፈጥሩ እገዛ ያደርጋል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...